አስገድዶ መሰወር ምንድን ነው? አስገድዶ መሰወር የሚያስከትላቸው የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች ወይም ሥጋቶች ምንድን ናቸው? ሰዎችን ከአስገድዶ መሰወር ለመጠበቅ የተዘረጉ የሕግ ማዕቀፎች ምንድን ናቸው? በመንግሥት ላይ የሚጥሏቸው ግዴታዎችስ?
የሰብአዊ መብቶች ምርመራ እና የወንጀል ምርመራ ሕጋዊና ተቋማዊ ማዕቀፎች ምንድን ናቸው? የሁለቱ የምርመራ ዐይነቶች ዓላማዎችና ግቦች ምንድን ናቸው? በሁለቱ የምርመራ ዘርፎች መካከል ያለው የማስረጃ ምዘና ስልት ልዩነት ምን ይመስላል? ሁለቱ የምርመራ ዘርፎች የሰብአዊ መብቶችን ጥበቃ ለማሻሻል በምን መንገድ ሊደጋገፉ ይችላሉ?
በቂ ምግብ የማግኘት መብት ምንድን ነው? በቂ ምግብ የማግኘት መብት ዋና ዋና ይዘቶች (Components) ምንድን ናቸው? በቂ ምግብ የማግኘት መብት ዓለም አቀፍ እና አህጉራዊ የሕግ ማዕቀፎች ምንድን ናቸው? የኢትዮጵያ የሕግ ማዕቀፍ ስለ ምግብ መብት ምን ደንግጓል? ከበቂ ምግብ የማግኘት መብት የሚመነጩ ግዴታዎች ምንድን ናቸው?
ጥሩ ሥራ (Decent Work) ምን ማለት ነው? የጥሩ ሥራ መመዘኛዎቹ ምንድናቸው? ጥሩ ሥራን ማስጠበቅ ምን ዐይነት ጠቀሜታ ይኖሩታል?
ሁለተኛ ደረጃ ጥቃት ምንድነው? ሁለተኛ ደረጃ ጥቃት ከመጀመሪያ ደረጃ ጥቃት በምን ይለያል? በሴቶችና ሕፃናት ላይ የሚደርስ ሁለተኛ ደረጃ ጥቃት መገለጫዎች ምንድን ናቸው?
ሕፃን ወታደሮች፣ ሕፃናትን በጦርነት ወይም በግጭት ውስጥ ማሳተፍ ምን ማለት ነው? ተፈጻሚነት ያላቸው ዓለም አቀፍ እና አህጉራዊ የሕግ ማዕቀፎች የትኞቹ ናቸው?
ኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ መብቶችን ያማከለ የሽግግር ፍትሕ ምንድነው? በሽግግር ፍትሕ ሂደት ኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ መብቶች እንዴት መካተት ይችላሉ?
በበጀት አመዳደብ ሂደት ሰብአዊ መብቶች ተኮር መሆን ማለት ሀብትን የሰው ልጆችን ባስቀደመ መልኩ ወይም ሰዎችን ማዕከል በሚያደርግ መንገድ መመደብ ነው
የንግድ ተግባራት በአግባቡ ካልተመሩ የጤና፣ የመኖሪያ ቤት፣ የምግብ፣ ውሃ፣ ማኅበራዊ ደኅንነት፣ የመሥራት መብት፣ ደኅንነቱ የተጠበቀ የሥራ ሁኔታ የማግኘት እንዲሁም የንግድ ማኅበራትን የመመሥረትና የመቀላቀል መብቶች አተገባበር ላይ ተጽዕኖ ይፈጥራሉ
ሰዎች በሰላም ወጥቶ የመግባት፣ ከቦታ ቦታ በነጻነት የመንቀሳቀስ እና የመሥራት መብቶቻቸው እንዲከበሩና መልካም እመርታዎች ዘላቂነት እንዲኖራቸው የትጥቅ ግጭቶችን ግልጽ እና አካታች በሆነ ሂደት ማስቆም፣ በቁርጠኝነት የሕግ የበላይነትን ማስከበር ይገባል