ለጊዜው ወይም ለዘለቄታው ከቤተሰቡ የተለየ ወይም ለራሱ ጥቅም ሲባል ከቤተሰቡ ጋር እንዲቆይ ሊደረግ የማይችል ሕፃን የመንግሥትን ልዩ ጥበቃ እና ድጋፍ የማግኘት መብት አለው
A child temporarily or permanently deprived of his or her family environment, or in whose own best interests cannot be allowed to remain in that environment, shall be entitled to special protection and assistance provided by the State
መንግሥት የተፈጥሮና ሰው ሠራሽ አደጋ እንዳይደርስ መከላከልና አደጋው ሲደርስም ለተጎጂው እርዳታ በወቅቱ እንዲደርስ ማድረግ አለበት
Government shall take measures to avert any natural and man-made disasters and, in the event of disasters, to provide timely assistance to the victims
አባል ሀገራት አረጋውያን ሴቶች ከጥቃት፣ ከወሲባዊ ጥቃት እንዲሁም በጾታ ላይ ከተመሠረተ መድልዎ መጠበቃቸውን ማረጋገጥ አለባቸው
States Parties shall ensure the protection of the rights of Older Women from violence, sexual abuse and discrimination based on gender
ማንኛውም ሰው ሐሳቡን የመግለጽ ነጻነት አለው
Everyone shall have the right to freedom of expression
ተመጣጣኝ ማመቻቸት በአካል ጉዳተኝነት ዐውድ ውስጥ ወዲያውኑ ተፈጻሚ ሊሆን የሚገባው አድሏዊ ልዩነት ያለማድረግ ግዴታ አካል ነው
Reasonable accommodation is an intrinsic part of the immediately applicable duty of non-discrimination in the context of disability