ወጣቶችን ጨምሮ በትጥቅ ግጭት የተጎዱ እና የተፈናቀሉ ሲቪል ሰዎችን ለመጠበቅ የሚቻላቸውን እርምጃ ሁሉ ይወስዳሉ
Take all feasible measures to protect the civilian population, including youth, who are affected and displaced by armed conflict
In the determination of any criminal charge against him, everyone shall be entitled to be tried in his presence, and to defend himself in person or through legal assistance of his own choosing
ማንኛውም ሰው በቀረበበት የወንጀል ክስ በተገኘበት የመዳኘት እና ራሱን በግሉ ወይም በመረጠው ጠበቃ በኩል የመከላከል፣ ጠበቃ ከሌለው ይህ መብት ያለው መሆኑ እንዲገለጽለት መብት አለው
ሴቶች ሠራተኞች ለተመሳሳይ ሥራ ተመሳሳይ ክፍያ የማግኘት መብታቸው የተጠበቀ ነው
Women workers have the right to equal pay for equal work
States shall have the duty, individually or collectively, to ensure the exercise of the right to development
ሀገራት በተናጠልም ሆነ በጋራ የልማት መብትን ተግባራዊነት የማረጋገጥ ግዴታ አለባቸው
የተ.መ.ድ. ጠቅላላ ጉባኤ የሁሉም ሰዎች የትምህርት መብትን እንዲሁም በሰብአዊነት ቀውስ ሁኔታ ውስጥ ደኅንነቱ የተጠበቀና አስቻይ የትምህርት ከባቢን እና በሁሉም ደረጃዎች የትምህርት ጥራትን የማስፈን አስፈላጊነትን  በድጋሚ ያረጋግጣል
The UN General Assembly reaffirms the right to education for all and the importance of ensuring safe enabling learning environments in humanitarian emergencies, as well as quality education at all levels