ስምምነቱ የሰብአዊ መብቶች እሴቶችን ወደ ማኅበረሰቡ ከማስረጽ አኳያ ተደራሽነትን በመጨመር በኢትዮጵያ ዘላቂና ውጤታማ በሆነ መንገድ የሰብአዊ መብቶች ባህልን ለማስፈን ከፍተኛ አስተዋፅዖ አለው
በየዓመቱ የሚከበረውን ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ቀንን ለማሰብ በኢሰመኮ አዘጋጅነት የተጀመረው የሰብአዊ መብቶች ፊልም ፌስቲቫል፤ በቀጣይ ዓመት በተመሳሳይ ወቅት ለሦስተኛ ዙር የሚመለስ ይሆናል
ሕዝባዊ የአቤቱታ መቀበያ መድረክ ግልጽ እና ሕዝባዊ ተሳትፎ የሚደረግበትና መብቶቻቸው የተጣሱ ተጎጂዎች፣ ምስክሮች፣ ሌሎች ባለድርሻ አካላት እንዲሁም የሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት በተገኙበት የሚከናወን የምርመራ ስልት ነው
ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ቀንን ለማሰብ እና የሰብአዊ መብቶች ግንዛቤ ለማዳበር ሰፊ ተደራሽነት ያለውን የፊልም ጥበብን በመጠቀም በሰብአዊ መብቶች ጉዳይ ላይ የሚያጠነጥኑ ፊልሞች ለእይታ እና ለውይይት ይቀርባሉ
በክልሉ በሲቪል ሰዎች ላይ እየደረሰ ያለው ግድያ፣ አካል ጉዳት እና መፈናቀል መጠነ ሰፊ ምርመራን ጨምሮ እየደረሰ ካለው ከፍተኛ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት ጋር የሚመጣጠን የፌዴራል መንግሥቱን አፋጣኝ እርምጃ እና ተጨባጭ ዘላቂ መፍትሔ የሚሻ ነው
የተሟላ አዲስ የሕግ ማዕቀፍ እንዲወጣ ወይም የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ እንዲሻሻል ያስፈልጋል
መንግሥት በኮንሶ ዞን እና በአጎራባች ልዩ ወረዳዎች ለሚገኙ ተፈናቃዮች የተደራጀ የምዝገባ ሥርዓት ማከናወን፣ የወሳኝ ኩነት አገልግሎትን ጨምሮ ሌሎች ሰነዶችን ማግኘት እንዲችሉ ማድረግ፣ እንዲሁም በክልሉ ለተደጋጋሚ መፈናቀል መንስዔ ለሆኑ ጉዳዮች ዘላቂ መፍትሔ ሊያፈላልግ ይገባል
የኮቪድ ወረርሽኝ፣ ድርቅ፣ ጦርነትና ግጭት ሳቢያ በሴቶችና ሕፃናት መሰረታዊ መብቶች ላይ ከፍተኛ ጫና ማሳደራቸውን ኮሚሽኑ ገልጿል
በካምፓላ ስምምነት ውስጥ የተካተቱ እና እንደ የሰነድና ምዝገባ፣ የጸጥታና ደኅንነት፣ የመንቀሳቀስ ነጻነት እና ፍትሕ የማግኘት መብት የመሳሰሉ መብቶችን እና በመንግሥት ላይ የተጣሉ ግዴታዎች ዙሪያ የተስተዋሉ ክፍተቶችን በማረም የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮችን የሰብአዊ መብቶች አያያዝ ማሻሻል ይገባል
ከሰኔ 7 እስከ ሰኔ 9 ቀን 2014 ዓ.ም. የተፈጸሙ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች ተጎጂዎች እና የተጎጂ ቤተሰቦች...