በግጭት ዐውድ ውስጥና ውጭ የሚፈጸሙ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶችንና ሥጋቶችን በአስቸኳይ ማቆምና የአማራና ኦሮሚያ ክልሎችን ጨምሮ ሁሉንም የትጥቅ ግጭቶች በውይይት በመፍታት ዘላቂ ሰላምና የሰብአዊ መብቶች መከበርን ማረጋገጥ ይገባል
በተፈጥሮ እና ሰው ሠራሽ ምክንያቶች ለሚከሰቱ መፈናቀሎች የሰብአዊ መብቶች መርሖችን የተከተለ ዘላቂ መፍትሔ ማመቻቸት ይገባል
የጥቆማ መስፈርቶቹ በኢሰመኮ መቋቋሚያ አዋጅ (በአዋጅ ቁጥር 1224/2012 እንደተሻሻለው) መሠረት ሲሆን፣ የጥቆማ ጊዜው እስከ ዐርብ ሚያዝያ 22 ቀን 2016 ዓ.ም. የሚቆይ ነው
በማሳደጊያ ተቋማት ውስጥ ለሚያድጉ ሕፃናት የሚሰጡ አገልግሎቶች እና እንክብካቤዎች በሕፃናት መብቶች የተቃኙ መሆን አለባቸው
የጥቃት ተጎጂ ሴቶች እና ሕፃናት በወንጀል ፍትሕ አስተዳደር ውስጥ ሲያልፉ መብቶቻቸውን በተሟላ መልኩ የሚያስጠብቁ ሕጎች እና አሠራሮች ያስፈልጋሉ
የፌዴራል እና የክልል መንግሥታት ነጻነታቸውን የተነፈጉ ሰዎች ሰብአዊ መብቶች ጥሰቶችን ለማስቆም፣ በጥሰቶች ተሳታፊ የሆኑ አጥፊዎችን ተጠያቂ ለማድረግ እና ለተጎጂዎች ተገቢ የሆነውን የካሳ ሥርዓት ለመዘርጋት ቁርጠኛ ሊሆኑ ይገባል
የፍትሕ ተቋማት ለአካል ጉዳተኞች እና አረጋውያን ተደራሽ ለመሆን ከከባቢያዊ፣ ከተቋማዊ፣ የመረጃና ተግባቦት እንዲሁም ከአመለካከት መሰናክሎች ነጻ መሆን አለባቸው
የጥፋተኞችን ተጠያቂነትን ከማረጋገጥ በተጨማሪ የማኅበረሰብ ውይይቶች፣ የሰላምና ዕርቅ ተጨባጭ እርምጃዎች ለዘላቂ መፍትሔ አስፈላጊ ናቸው
በሲቪል ሰዎች ላይ የሚደርሱ ግድያዎችንና ሌሎች የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶችን ማቆም፣ ተጠያቂነት ማረጋገጥ፣ ተጎጂዎችን መካስ እና ለዘላቂ መፍትሔ በሁሉም ወገኖች ሰላማዊ ውይይትን በቁርጠኝነት መቀበል ይገባል
ዘላቂ መፍትሔ እስኪረጋገጥ ድረስ ተፈናቃዮች በቂ፣ ወቅቱን የጠበቀ እና ተደራሽ የሆነ የሰብአዊ ድጋፍ ሊቀርብላቸው እንዲሁም በቂ መጠለያ ሊመቻችላቸው ይገባል