የፌዴራል እና የሁለቱ ክልሎች መንግሥታት በአፋጣኝ በመረጃና በምዝገባ ሥርዓት የታገዘ፣ አሳታፊ የሆነ፣ የተጠያቂነት ሥርዓት የተዘረጋለት እንዲሁም ከፍላጎት ጋር የተመጣጠነ ምላሽ ማቅረብ እና ክትትል ማድረግ፣ እንዲሁም በትምህርት፣ በጤና ግልጋሎት እና በመጠለያ መብት ረገድ ያለውን ክፍተት በመለየት መብቶቹን ለማሟላት ተገቢውን እርምጃ በአፋጣኝ መውሰድ እና በመንግሥትና በአጋር ድርጅቶች ለድርቁ የሚሰጡ ምላሾች ለሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች ተጋላጭ የሆኑ የማኅበረሰብ ክፍሎችን ልዩ ፍላጎቶች ከግምት ውስጥ ያስገቡ እንዲሆኑ ማድረግ ይኖርባቸዋል
The report covers the period between June 2021 and June 2022 (Ethiopian fiscal year) and consists of an overall assessment of the human rights situation in the country; key positive developments, main concerns, challenges and recommendations
ሪፖርቱ የሚሸፍነው ጊዜ በኢትዮጵያ የበጀት ዓመት አቆጣጠር መሰረት ከሰኔ ወር 2013 ዓ.ም. እስከ ሰኔ ወር 2014 ዓ.ም. ያሉትን 12 ወራት ሲሆን፣ በዓመቱ ውስጥ የነበረውን አጠቃላይ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታን፣ የተገኙ ቁልፍ እመርታዎችን፣ ዋና ዋና አሳሳቢ ጉዳዮችን፣ ተግዳሮቶችን እና ምክረ-ሃሳቦችን ያካትታል
በብሔር ማንነት ላይ የተመሰረተ ሕገ ወጥ እና የዘፈቀደ እስር በመሆኑ በአፋጣኝ ሊለቀቁ ይገባል፤ ወደ መኖሪያ አካባቢያቸውም እስኪመለሱ ድረስ በካምፑ ውስጥ ለመቆየት የሚፈልጉ ሰዎች ቢኖሩ በሙሉ ፈቃደኝነትና ያለ ማናቸውም ዓይነት የእንቅስቃሴ ገደብ ሊሆን ይገባል
የተራዘመ ቅድመ-ክስ እስር (prolonged pre-trial detention) ሰዎች በፍትሕ አስተዳደር ላይ ያላቸውን እምነት ያጠፋል
የክልሉ መንግሥት ለሟች ቤተሰቦች እና የአካል ጉዳት ለደረሰባቸው ሰዎች ካሳ የከፈለ ቢሆንም ለተሟላ ፍትሕ የወንጀል ተጠያቂነት ሊረጋገጥ ይገባል
ፍትሕ እና የተጎዱ ሰዎችና ቦታዎችን መልሶ መጠገን የሁሉንም ወገኖች ቁርጠኝነት ይፈልጋል
Strong commitment of all actors indispensable to obtain justice for victims and rehabilitation of areas affected by the conflict
ለሟቾች ቤተሰቦች እና የአካል ጉዳት ለደረሰባቸው ሰዎች ለደረሰባቸው ጉዳት ተገቢ የሆነ ካሳ ሊሰጣቸው ይገባል
የተፈጸሙ ጥሰቶች የጦር ወንጀል ስለመሆናቸው አመላካች ሁኔታዎች አሉ