EHRC Chief Commissioner Daniel Bekele intervention at the Interactive Dialogue on Ethiopia at the 52nd Session of the United Nations Human Rights Council. ID on Report of the International Commission of Human Rights Experts on Ethiopia (oral briefing, res. 51/27 21) March 22, 2023
ክትትሉ በዋናነት ያተኮረው በማእከላቱ አደረጃጀት፣ በተጠቃሚዎች ልየታ ሥርዓት፣ በአገልግሎት ዓይነቶች እና በሰብአዊ መብቶች አያያዝ ሁኔታ ላይ ሲሆን፤ አግባብነት ካላቸው ዓለም አቀፍ፣ አህጉራዊ እና ሀገራዊ ሕጎች እና መርሆች አንጻር በመገምገም ምክረ ሐሳቦችን ይሰጣል፡፡ በዚህ ክፍል የክትትሉ አንኳር ጉዳዮች እና ምክረ ሐሳቦች እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ/ኮሚሽኑ) በሕግ ከተሰጡት ሥልጣን፣ ተግባርና ኃላፊነቶች መካከል የሰብአዊ መብቶች ክትትል ማድረግ አንዱ በመሆኑ በተለይ ለሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች ተጋላጭ የሆኑ የሕብረተሰብ ክፍሎችን ታሳቢ ያደረጉ የክትትል ሥራዎችን ያከናውናል፡፡ አረጋውያን ከዕድሜ መግፋት ጋር ተያይዘው ለሚመጡ አድሎዎች እና ለሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች ተጋላጭ በመሆናቸው እና የሚያስፈልጋቸውን ድጋፍ ለመስጠት ሲባል አረጋውያንን በአንድ ማእከል ውስጥ አሰባስቦ እንክብካቤ መስጠት...
This Advisory Note on Transitional Justice prepared by the Ethiopian Human Rights Commission and the United Nations Office of the High Commissioner for Human Rights presents the preliminary findings of thirteen community consultations held on transitional justice with over 700 individuals in several regions of Ethiopia, between July and December 2022. In addition to presenting...
የሕፃናት የተሳትፎ መብት ሕፃናት በሚመለከታቸው ጉዳዮች ላይ ሃሳባቸውን ከመግለጽ እና ከመሰማት መብት ጋር የሚያያዝ ነው፡፡ የተባበሩት መንግሥታት የሕፃናት መብቶች ኮሚቴ እ.ኤ.አ. በ2009 በሰጠው ጠቅላላ ትንታኔ የሕፃናት ሃሳባቸውን የመግለጽ ችሎታ፣ በሚመለከታቸው ጉዳዮች ላይ ሃሳብ የመስጠት፣ ዕድሜያቸውን እና ብስለታቸውን ባገናዘበ መንገድ የሚሰጡት ሃሳብ ክብደት እንዲሰጠው እንዲሁም በመንግሥታዊም ሆነ በግል ተቋማት ውስጥ የመሳተፍ ሰብአዊ መብት እንዳላቸው ያስቀምጣል፡፡ መንግሥታትም...
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ/ኮሚሽኑ) የተፈናቃዮች የሰብአዊ መብቶች አያያዝ ያለበትን ሁኔታ ለመረዳት፤ የመፈናቀሉ አውድ እና መንስኤዎች፣ በመፈናቀል ወቅት ያጋጠሙ አንኳር የሰብአዊ መብቶች አያያዝ ክፍተቶች እና የሰብአዊ ድጋፍ ፍላጎቶችን ለመለየት ከሐምሌ 24 እስከ ነሐሴ 6 ቀን 2014 ዓ.ም. በደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች (ደ/ብ/ብ/ሕ) ክልል በኮንሶ ዞን፣ በአሌ ልዩ ወረዳ፣ በዲራሼ ልዩ ወረዳ እና በአማሮ ልዩ...
ይህ ዓመታዊ የሴቶችና የሕፃናት መብቶች የዘርፍ ሪፖርት ከመስከረም 2014 ዓ.ም. እስከ ነሐሴ 2014 ዓ.ም. ያለውን ጊዜ የሚሸፍን ሲሆን ኢሰመኮ ሐምሌ 1 ቀን 2014 ዓ.ም. ይፋ ካደረገው አጠቃላይ የኢትዮጵያ ዓመታዊ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ሪፖርት በተጨማሪነት በተለይ የሴቶችና የሕፃናት ሰብአዊ መብቶች አያያዝ ላይ በዝርዝር በማተኮር ኮሚሽኑ የለያቸውን አበረታች እመርታዎችን፣ ዋና ዋና አሳሳቢ ጉዳዮችን እና ምክረ-ሃሳቦችን አካቷል፡፡ ኮሚሽኑ...
(Download the English version below) ⬇️ ይህ ዓመታዊ የዘርፍ ሪፖርት ኢሰመኮ በሐምሌ 1 ቀን 2014 ዓ.ም. ይፋ ካደረገው የኢትዮጵያ ዓመታዊ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ሪፖርት ላይ በተጨማሪነት በተለይ በሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች ሰብአዊ መብቶች አያያዝ ላይ በዝርዝር በማተኮር ባለፈው የበጀት ዓመት ኮሚሽኑ ባከናወናቸው ልዩ ልዩ ተግባራት የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች የሰብአዊ መብቶች አያያዝን በተመለከተ የለያቸውን መልካም ጅማሮዎች፣ አሳሳቢ...
ይህ ቻርተር ከአሕጉራችን የሰብአዊ መብት ሰነዶች ቀዳሚው ነው፡፡ ይህን ቻርተር ፈርመው የተቀበሉ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት አባል ሀገራት በዚህ ቻርተር የተደነገጉትን መብቶች፣ ግዴታዎችና ነጻነቶች አውቀው በመቀበል ለተግባራዊነታቸው ሕግ ለማውጣትና ሌሎች እርምጃዎችን ለመውሰድ ግዴታ ገብተዋል፡፡
የአፍሪካ ሕፃናት መብቶችና ደኅንነት ቻርተር፡፡ የቻርተሩ ተዋዋይ ሀገራት የሆኑ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት አባል ሀገራት በቻርተሩ ለተደነገጉ መብቶች፣ ነጻነቶችና ግዴታዎች ዕውቅና የመስጠት የቻርተሩ ድንጋጌዎችን ተፈጻሚ ለማድረግ በቻርተሩና በየሕገ-መንግሥቶቻቸው በተመለከቱ ድንጋጌዎች መሰረት እንደ አስፈላጊነቱ የሕግ ማውጣትን እና ሌሎች እርምጃዎች የመውሰድ ግዴታ አለባቸው፡፡