የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን የኦሞ ወንዝ ከመጠን በላይ በመሙላቱ እና መደበኛ የመፍሰሻ መስመሩን ለቆ በመውጣቱ ምክንያት በጎርፍ ከተጥለቀለቁ የወንዙ የታችኛው ተፋሰስ አካባቢዎች በተለይም ከዳሰነች ወረዳ የተፈናቀሉ ሰዎችን የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ አስመልክቶ ከጥቅምት 5 እስከ 20 ቀን 2016 ዓ.ም. ክትትል በማከናወን ያዘጋጀውን ባለ 26 ገጽ ሪፖርት ይፋ አድርጓል፡፡ ኢሰመኮ...
በአፍሪካ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች ጥበቃና ድጋፍን አስመልክቶ የተደረገ የአፍሪካ ኅብረት ስምምነት (የካምፓላ ስምምነት)
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ከሰኔ ወር 2014 ዓ.ም. እስከ ሰኔ ወር 2015 ዓ.ም. ድረስ ያለውን ጊዜ የሚሸፍን ሁለተኛውን የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች ሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ዓመታዊ ባለ 60 ገጽ ሪፖርት ይፋ አድርጓል፡፡ ይህ ሁለተኛው የዘርፍ ሪፖርት ኢሰመኮ ሐምሌ 5 ቀን 2015 ዓ.ም. ይፋ ካደረገው የኢትዮጵያ ዓመታዊ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ሪፖርት ላይ በተጨማሪነት ኮሚሽኑ የተፈናቃዮች የሰብአዊ...
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ/ኮሚሽኑ) ሁለተኛውን ዓመታዊ የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ሪፖርት ሐምሌ 5 ቀን 2015 ዓ.ም. ለሕዝብ ይፋ ማድረጉ ይታወሳል፡፡ ኮሚሽኑ ሪፖርቱን ይፋ ሲያደርግ፣ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች ሰብአዊ መብቶች አያያዝን በተመለከተ በ2015 ዓ.ም. ኮሚሽኑ ባከናወናቸው የክትትልና የምርመራ ሥራዎች የለያቸውን አሳሳቢ ጉዳዮች ለማስተካከል የተሰጡ ምክረ ሐሳቦች ተፈጻሚ እንዲሆኑ እንዲሁም የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ውሳኔዎችን ከመስጠታቸው በፊት...
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ/ኮሚሽኑ) የተፈናቃዮች የሰብአዊ መብቶች አያያዝ ያለበትን ሁኔታ ለመረዳት፤ የመፈናቀሉ አውድ እና መንስኤዎች፣ በመፈናቀል ወቅት ያጋጠሙ አንኳር የሰብአዊ መብቶች አያያዝ ክፍተቶች እና የሰብአዊ ድጋፍ ፍላጎቶችን ለመለየት ከሐምሌ 24 እስከ ነሐሴ 6 ቀን 2014 ዓ.ም. በደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች (ደ/ብ/ብ/ሕ) ክልል በኮንሶ ዞን፣ በአሌ ልዩ ወረዳ፣ በዲራሼ ልዩ ወረዳ እና በአማሮ ልዩ...
(Download the English version below) ⬇️ ይህ ዓመታዊ የዘርፍ ሪፖርት ኢሰመኮ በሐምሌ 1 ቀን 2014 ዓ.ም. ይፋ ካደረገው የኢትዮጵያ ዓመታዊ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ሪፖርት ላይ በተጨማሪነት በተለይ በሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች ሰብአዊ መብቶች አያያዝ ላይ በዝርዝር በማተኮር ባለፈው የበጀት ዓመት ኮሚሽኑ ባከናወናቸው ልዩ ልዩ ተግባራት የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች የሰብአዊ መብቶች አያያዝን በተመለከተ የለያቸውን መልካም ጅማሮዎች፣ አሳሳቢ...