መገናኛ ብዙኃን የሚመሩባቸው ሕጎችና ፖሊሲዎች፣ የሚከተሏቸው አሠራሮች እንዲሁም የሚያሰራጯቸው ይዘቶች የሴቶች መብቶች እንዲጠበቁ ወይም በተቃራኒው እንዲሸረሸሩ በማድረግ ረገድ ያላቸው ሚና የጎላ ነው። መንግሥት የሴቶችን መብቶች ተግባራዊነት ለማረጋገጥ በተለይም ሁሉም መገናኛ ብዙኃን በሴቶች ላይ የሚደርሱ መድልዎ እና አግላይ አስተሳሰቦችን፣ አገላለጾችን፣ አሠራሮችንና ይዘቶችን እንዲያስወግዱ ለማበረታታት ውጤታማ እርምጃዎችን መውሰድ አለበት፡፡ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በሴቶች መብቶች ሁኔታዎች...