የተ.መ.ድ. ጠቅላላ ጉባኤ እ.ኤ.አ. 1993 የፕሬስ ነጻነት ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ እንዲከበር ያስተላለፈውን ውሳኔ ተከትሎ በየዓመቱ እ.ኤ.አ. ግንቦት 3 ቀን ዓለም አቀፍ የፕሬስ ነጻነት ቀን ይከበራል። በዚህ ዓመት ትኩረቱን ሰው ሠራሽ አስተውሎት (Artificial intelligence) በፕሬስ ነጻነት እና በመገናኛ ብዙኃን ላይ እያሳደረ ያለው ተጽዕኖ ላይ በማድረግ ፖሊሲ አውጪዎችን፣ ጋዜጠኞችን፣ የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎችን እና የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች...