የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በቀድሞው ደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልላዊ መንግሥት የሚገኙ 6 ዞኖች (ጋሞ፣ ጌዴኦ፣ ጎፋ፣ ኮንሶ፣ ደቡብ ኦሞ እና ወላይታ) እና 5 ልዩ ወረዳዎች (አሌ፣ አማሮ፣ ባስኬቶ፣ ቡርጂ እና ዲራሼ) የተደረገ ሕዝበ ውሳኔ እንዲሁም በወላይታ ዞን የተደረገ ድጋሚ ሕዝበ ውሳኔ ላይ ያከናወነውን የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ክትትል ባለ 50 ገጽ ሪፖርት ይፋ አድርጓል።...
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ/ኮሚሽኑ) በሕግ ከተሰጡት ሥልጣን እና ኃላፊነቶች መካከል አንዱ በምርጫ ወቅት የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ክትትል ማድረግ በመሆኑ በቀድሞው ደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልላዊ መንግሥት (የቀድሞው ደቡብ ክልል) ጥር 29 ቀን 2015 ዓ.ም. የተደረገ ሕዝበ ውሳኔ እንዲሁም በወላይታ ዞን ሰኔ 12 ቀን 2015 ዓ.ም. የተደረገ ድጋሚ ሕዝበ ውሳኔ ሂደትን የሰብአዊ መብቶች ክትትል አድርጓል።...