የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን የኦሞ ወንዝ ከመጠን በላይ በመሙላቱ እና መደበኛ የመፍሰሻ መስመሩን ለቆ በመውጣቱ ምክንያት በጎርፍ ከተጥለቀለቁ የወንዙ የታችኛው ተፋሰስ አካባቢዎች በተለይም ከዳሰነች ወረዳ የተፈናቀሉ ሰዎችን የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ አስመልክቶ ከጥቅምት 5 እስከ 20 ቀን 2016 ዓ.ም. ክትትል በማከናወን ያዘጋጀውን ባለ 26 ገጽ ሪፖርት ይፋ አድርጓል፡፡ ኢሰመኮ...