የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በማእከላዊ ኢትዮጵያ እና በደቡብ ኢትዮጵያ ክልሎች በተለይም ከአዳዲስ የክልል አደረጃጀቶችና መዋቅሮች መቋቋም ወይም ተያያዥ ውሳኔዎች ጋር በተያያዘ የሚነሱ የደመወዝ መዘግየትን እና ያለመከፈልን የተመለከቱ አቤቱታዎችን እና ጥቆማዎችን መነሻ በማድረግ የሰብአዊ መብቶች ምርመራ በማከናወን ታኅሣሥ 13 ቀን 2016 ዓ.ም. ሪፖርት (ከዚህ በኋላ “ዋናው የምርመራ ሪፖርት”) ይፋ ማድረጉ ይታወቃል። በዚሁ መሠረት፣ ከ2012 ዓ.ም....