






የብሮድካስት አገልግሎት ከሌሎች የመገናኛ ብዙኃን አውታሮች በተለየ፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለአንድ ሀገር የተመደበውን ውስን ሞገድ የሚጠቀም በመሆኑ፤ ከሌሎች ምክንያቶች በተጨማሪ ይህን ውስን ሃብት ብሎም ዘርፉን የሚያስተዳድር የሕግና የፖሊሲ ማዕቀፍ ያስፈልጋል፡፡ ነፃነቱ የተጠበቀ ተቋም ማደራጀት፣ ግልጽና ገለልተኛ የፈቃድ አሰጣጥና እድሳት ሥርዓት መዘርጋት፣ ባለቤትነትንና ብዝኃነትን መወሰን፣ የይዘት ክትትል ሥርዓትን መደንገግ፣ የፕሮግራም ደረጃ ማስቀመጥ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት...