ኢትዮጵያ የዓለም አቀፍ የአካል ጉዳተኞች መብቶች ስምምነትን በአዋጅ ቁጥር 676/2002 ተቀብላ አጽድቃለች። ይህንን ስምምነት የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ኢትዮጵያ የተቀበለቻቸውን ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ሰነዶችን በሀገር ውስጥ ቋንቋዎች ለመተርጎምና ለማሰራጨት በአዋጅ ቁጥር 210/1992 (በአዋጅ ቁጥር 1224/2012 እንደተሻሻለው) አንቀጽ 6(8) በተሰጠው ስልጣን መሠረት ወደ አማርኛ ቋንቋ አስተርጉሞ አሳትሟል።
ኢትዮጵያ የአፍሪካ የሰዎችና ሕዝቦች መብቶች ቻርተር የአረጋውያን መብቶች ፕሮቶኮል በአዋጅ ቁጥር 1182/2012ተቀብላ አጽድቃለች። ይህንን ፕሮቶኮል የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ኢትዮጵያ የተቀበለቻቸውን ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ሰነዶችን በሀገር ውስጥ ቋንቋዎች ለመተርጎምና ለማሰራጨት በአዋጅ ቁጥር 210/1992 (በአዋጅ ቁጥር 1224/2012 እንደተሻሻለው) አንቀጽ 6(8) በተሰጠው ስልጣን መሠረት ወደ አማርኛ ቋንቋ አስተርጉሞ አሳትሟል።