- Version
- Download 208
- File Size 185.47 KB
- File Count 1
- Create Date August 4, 2023
- Last Updated August 21, 2023
ማብራሪያ:- በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ወቅት ሊጠበቁ የሚገባቸው የሰብአዊ መብቶች ድንጋጌዎች እና መርሖች
የሕግ አስከባሪ ተቋማት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁንና ደንቡን በሥራ ላይ ሲያውሉ እና ሲያስፈጽሙ ከዚህ በታች በተመለከቱት የሰብአዊ መብቶች እና ሕገ መንግሥታዊ መርሖች እንዲመሩ፣ በማናቸውም ሁኔታ ሊገደቡ የማይችሉ መሠረታዊ መብቶችን እንዲያከብሩና እንዲያስከብሩ፣ እንዲሁም በከፍተኛ የኃላፊነት ስሜትና የሙያ ሥነ ምግባር እንዲመሩ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን በከፍተኛ አደራ ጭምር እያሳሰበ አፈጻጸሙንም በስልታዊ መንገድ የሚከታተል መሆኑን ይገልጻል፡፡