Download
Download is available until [expire_date]
  • Version
  • Download 73
  • File Size 214.51 KB
  • File Count 1
  • Create Date December 13, 2022
  • Last Updated December 13, 2022

ማብራሪያ:- የሕፃናትን በሚመለከቷቸው ጉዳዮች ላይ ተሳትፎ የማድረግ ሰብአዊ መብት እንዴት ማሟላት ይቻላል?

የሕፃናት የተሳትፎ መብት ሕፃናት በሚመለከታቸው ጉዳዮች ላይ ሃሳባቸውን ከመግለጽ እና ከመሰማት መብት ጋር የሚያያዝ ነው፡፡ የተባበሩት መንግሥታት የሕፃናት መብቶች ኮሚቴ እ.ኤ.አ. በ2009 በሰጠው ጠቅላላ ትንታኔ የሕፃናት ሃሳባቸውን የመግለጽ ችሎታ፣ በሚመለከታቸው ጉዳዮች ላይ ሃሳብ የመስጠት፣ ዕድሜያቸውን እና ብስለታቸውን ባገናዘበ መንገድ የሚሰጡት ሃሳብ ክብደት እንዲሰጠው እንዲሁም በመንግሥታዊም ሆነ በግል ተቋማት ውስጥ የመሳተፍ ሰብአዊ መብት እንዳላቸው ያስቀምጣል፡፡ መንግሥታትም ትርጉም ባለው መንገድ ሕፃናትን በሚመለከታቸው ጉዳይ ላይ የማሳተፍ ግዴታ ያለባቸው ሲሆን ይህን መብታቸውን ለማረጋገጥ አስፈላጊውን እርምጃዎች መውሰድ እንዳለባቸውም አስገንዝቧል፡፡

በዚህ መሠረት ሕፃናት በትምህርት ቤት፣ በቤተሰብ ውስጥ፣ በማኅበራዊ፣ መንግሥታዊ እና ሌሎች ተቋማት እነርሱን በሚመለከቱ ማናቸውም ጉዳዮች ላይ በቀጥታ ራሳቸው ወይም በተወካዮቻቸው ወይም በሚመለከተው አካል አማካይነት ሃሳባቸውን እንዲገልጹ እና ድምፃቸው እንዲሰማ ዕድል የማግኘት ሰብአዊ መብቶች ያሏቸው ሲሆን እነዚህ መብቶች በአጠቃላይ የሕፃናት የተሳትፎ መብቶች በሚል ሊጠቀሱ የሚችሉ ናቸው፡፡