- Version
- Download 349
- File Size 195.25 KB
- File Count 1
- Create Date May 21, 2021
- Last Updated May 21, 2021
ጥቅምት 21 ቀን 2013 ዓ.ም. ኮንሶ ዞን አካባቢ የሚገኘው የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት አካባቢውን ለቅቆ መውጣቱን ተከትሎ፣ከኅዳር 1 እስከ ኅዳር 11 ቀን 2013 ዓ.ም. ድረስ በአሌ፣ በኮንሶ ዞን በሰገን ዙሪያ ወረዳ ውስጥ በሚገኙ ቀበሌዎች፣ በአማሮ ወረዳ ቡኒቲ ቀበሌ፣ እንዲሁም ከኅዳር 6 እስከ ኅዳር 8 ቀን 2013 ዓ.ም. በደራሼ ወረዳ ጋቶ ቀበሌ ተከታታይ ግጭቶች ዳግም ተከስተዋል። የደቡብ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ በሰገን አከባቢ በተፈጠረው የፀጥታ መደፍረስ እና ግጭት 66 ሰዎች መገደላቸውን፣ 39 ሰዎች መቁሰላቸውን እንዲሁም 132 ሺህ 142 ሰዎች መፈናቀላቸውን አስታውቋል። የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ/ኮሚሽኑ) ከኅዳር 12 ቀን እስከ ኅዳር 16 ቀን 2013 ዓ.ም. ወደ አካባቢው የክትትል ቡድን ልኮ ምርምራ አድርጓል።