Download
Download is available until [expire_date]
  • Version
  • Download 321
  • File Size 863.07 KB
  • File Count 1
  • Create Date August 12, 2023
  • Last Updated August 21, 2023

አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቁጥር 62015 በተመለከተ ከኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) የተሰጠ ምክረ ሐሳብ

በማንኛውም ምክንያት ቢሆን የሚታወጅ የአስቸኳይ ጊዜ ሁኔታ ለሰብአዊ መብቶች አያያዝ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ የሚያሳድር ነው። ኢሰመኮ በተለያዩ ወቅቶች በሀገሪቱ በከፊልም ሆነ በሀገር አቀፍ የተጣሉ የአስቸኳይ ጊዜ ሁኔታዎች በመቋቋሚያ አዋጁ በተጣለበት ኃላፊነት መሠረት ክትትል እና ምርመራ አድርጎ፣ ሪፖርቱን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና  ለሕዝብ ይፋ ማድረጉ የሚታወስ ነው።

በእነዚህ የክትትል እና የምርመራ ግኝቶቹም መሠረት ከዚህ ቀደም በነበሩ የአስቸኳይ ጊዜ ሁኔታዎች ወቅት የተለያዩ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች መድረሳቸውን አስረድቷል፡፡ ከእነዚህም መካከል ኢሰብአዊ አያያዞች፣ በተለይም በጥቆማ ላይ የተመሠረቱ እስሮችን በተመለከተ የጥቆማዎቹ መነሻ የሰዎቹ የብሔር ማንነት አለመሆኑን ለማረጋገጥ እና ምክንያታዊ ጥርጣሬ ስለመኖሩ ለማጣራት በቂ ጥረት ያልተደረገባቸው በርካታ እስሮች እንደነበሩ፣ ሴቶች፣ አረጋውያን እና አካል ጉዳተኞች እና በመገናኛ ብዙኃን ባለሞያዎች ላይ የደረሱ ጥሰቶች ዋነኞቹ ናቸው።

ጠቅለል ባለ መልኩ ምክረ ሐሳቦቹ የሚከተሉትን ሦስት መሠረታዊ ነጥቦች አንስተዋል:-

1/ የአስቸኳይ ጊዜ ሁኔታ ለማወጅ የጥብቅ አስፈላጊነት እና ተመጣጣኝነት መርሖች መሟላታቸውን በበቂ ሁኔታ ማረጋገጥ፣ በአንድ በኩል የተከሰተውን የጸጥታ ሁኔታ ለማሻሻል እና ለማስቆም የሚረዱ ሁሉም የሕግ አማራጮች መታየታቸውን እንዲሁም በሀገር አቀፍ ደረጃ ተፈጻሚነት ሊኖረው የሚችል እና እያንዳንዱ በአዋጁ የተዘረዘሩ እገዳዎች እና ክልከላዎች የጥብቅ አስፈላጊነት እና ተመጣጣኝነትን መርሖች ማሟላታቸውን ማረጋገጥ፣ 

2/ ለአሻሚ ትርጓሜ ወይም ተገቢ ላልሆነ አጠቃቀም ክፍት በመሆናቸው ለሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች፣ ሥልጣንን አላግባብ ለመጠቀም እና ለተለያዩ የመንግሥት አካላት ሥልጣን መጋፋት/መሻማት የሚዳርጉ ቃላቶች፣ ሐረጎች እና አንቀጾች እንዲሰረዙ አልያም እንዲሻሻሉ፣  

3/ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት (parliamentary oversight) የአስቸኳይ ጊዜ እርምጃዎች ክትትል አስፈላጊነት፣ የዳኝነት ነጻነትና ዋስትና አስፈላጊነትና የኮሚሽኑን የሰብአዊ መብቶች ክትትል አስፈላጊነት እንዲሁም የሕዝብ ተወካዮችንና የዳኞችን ልዩ መብቶች (Immunity) የሚመለከቱ ጉዳዮች ያካተቱ ምክረ ሐሳቦችን ምክር ቤቱና መንግሥት በጥንቃቄ አጢኖ ተግባራዊ እንዲያደርገቸው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ያሳስባል፡፡