- Version
- Download 30
- File Size 389.01 KB
- File Count 1
- Create Date April 9, 2024
- Last Updated April 9, 2024
አንኳር ጉዳዮች:- በአዲስ አበባ፣ በድሬዳዋ እና በአምስት ክልሎች በሚገኙ የሕፃናት ማሳደጊያ ተቋማት ላይ የተከናወነ የሰብአዊ መብቶች ክትትል ሪፖርት
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በአምስት ክልሎች እና በሁለት የከተማ አስተዳድሮች በሚገኙ የመንግሥት እና መንግሥታዊ ባልሆኑ የሕፃናት ማሳደጊያ ተቋማት ውስጥ ያሉ ሕፃናት የሰብአዊ መብቶች ሁኔታን የተመለከተ ባለ 45 ገጽ የክትትል ሪፖርት ይፋ አድርጓል። ኮሚሽኑ በአማራ፣ በሐረሪ፣ በኦሮሚያ፣ በሲዳማ እና በደቡብ ኢትዮጵያ ክልሎች እንዲሁም በአዲስ አበባ እና በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደሮች በሚገኙ 25 የሕፃናት ማሳደጊያ ተቋማት ላይ ከመጋቢት 11 እስከ 19 ቀን 2015 ዓ.ም. የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ክትትል አከናውኗል።
በክትትሉ በአጠቃላይ ከ394 ሰዎች ጋር ቃለ መጠይቅ ተደርጓል፤ ከእነዚህም መካከል 250 ሕፃናት፣ 23 የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች እና 121 የማሳደጊያ ተቋማት ኃላፊዎች እና ባለሙያዎች በቃለ መጠይቁ ተሳትፈዋል። ኮሚሽኑ 25 የቡድን ውይይቶችን በማሳደጊያ ተቋማት ከሚኖሩ ሕፃናት ጋር እና 17 የቡድን ውይይቶችን ደግሞ ከተቋማቱ ሠራተኞች ጋር በአጠቃላይ 42 የቡድን ውይይቶችን አከናውኗል። የአካል ምልከታም በየተቋማቱ በማድረግ እና ጠቃሚ ሰነዶችን በመመርመር መረጃ እና ማስረጃዎች ተሰብስቧል። በሪፖርቱ የክትትሉ ግኝቶች፣ መልካም ተሞክሮዎች እንዲሁም በማሳደጊያ ተቋማት ውስጥ ለሕፃናት የሚሰጡ አገልግሎቶችን እና ጥበቃዎችን ለማሻሻል የሚያስችሉ ዝርዝር ምክረ ሐሳቦች ቀርበዋል።
በአዲስ አበባ፣ በድሬዳዋ እና በአምስት ክልሎች በሚገኙ የሕፃናት ማሳደጊያ ተቋማት ላይ የተከናወነ የሰብአዊ መብቶች ክትትል ሪፖርት