- Version
- Download 25
- File Size 433.38 KB
- File Count 1
- Create Date June 9, 2023
- Last Updated August 21, 2023
አንኳር ጉዳዮች:- በግሉ የጤና ዘርፍ የሚሰጡ አገልግሎቶች ለሕብረተሰቡ ያላቸው የፋይናንስ ተደራሽነት እና የጤና መብት አተገባበር ክትትል ሪፖርት
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) የግሉ የጤና ዘርፍ ከሕብረተሰቡ የመክፈል ዐቅም ጋር የተመጣጠነ እና ተደራሽ የሆነ አገልግሎት አቅርቦት ላይ ያተኮረ ባለ 39 ገጽ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ክትትል ሪፖርት ይፋ አድርጓል።
የጤና መብት ተገኝነት፣ ተደራሽነት፣ ተቀባይነት እና ጥራት ላይ ያተኮሩ አራት ዋና ዋና ይዘቶች ያሉት ሲሆን ክትትሉ በተደራሽነት (accessibility) ሥር ከተጠቃለሉት ንዑስ ይዘቶች መካከል በገንዘብ ተደራሽነት ላይ ትኩረት በማድረግ መከናወኑ በሪፖርቱ ተብራርቷል። ሪፖርቱን ለማዘጋጀት በአጠቃላይ ከ218 የባለድርሻ አካላት (80 የግል የጤና ተቋማት ኀላፊዎች፣ 8 መንግሥታዊ ያልሆኑ የጤና አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማት ተጠሪዎች፣ 20 የመንግሥት ተቋማት ኀላፊዎች፣ 80 የግል የጤና ተቋማት ተጠቃሚዎች/ተገልጋዮች እና 30 የምክክር መድረክ ተሳታፊዎች) ከሃዋሳ፣ ከባሕር ዳር፣ ከአዲስ አበባ እና ከጅማ ከተሞች መረጃዎች ተሰብስበዋል።
በግሉ የጤና ዘርፍ የሚሰጡ አገልግሎቶች ለሕብረተሰቡ ያላቸው የፋይናንስ ተደራሽነት እና የጤና መብት አተገባበር ክትትል ሪፖርት