- Version
- Download 1
- File Size 884.73 KB
- File Count 1
- Create Date March 16, 2026
- Last Updated March 16, 2026
የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ዓመታዊ ሪፖርት
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮችን ሰብአዊ መብቶች አንዱ የትኩረት አቅጣጫ በማድረግ ላለፉት 5 ዓመታት ወቅታዊ እና ቀጣይነት ያላቸው የሰብአዊ መብቶች ክትትል እና ምርመራ፣ የግንዛቤ ማሳደግ እንዲሁም የውትወታ ሥራዎችን ሲያከናውን ቆይቷል። ይህ የኢሰመኮ አራተኛው በሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች ሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ላይ ያተኮረ ዓመታዊ የዘርፍ ሪፖርት ሲሆን፣ ከሐምሌ ወር 2016 ዓ.ም. እስከ ሰኔ ወር 2017 ዓ.ም. ድረስ ያለውን ጊዜ ይሸፍናል። ኢሰመኮ በሐምሌ 28 ቀን 2017 ዓ.ም. ይፋ ካደረገው አራተኛው የኢትዮጵያ ዓመታዊ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ሪፖርት በተጨማሪ በበጀት ዓመቱ ባከናወናቸው ልዩ ልዩ ተግባራት፣ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች ሰብአዊ መብቶች ሁኔታን በተመለከተ የለያቸውን መልካም ጅማሮዎች፣ አሳሳቢ ሁኔታዎችን እንዲሁም በሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ሊተገበሩ የሚገባቸውን ምክረ ሐሳቦች አካቷል።
