- Version
- Download 1
- File Size 884.73 KB
- File Count 1
- Create Date March 16, 2026
- Last Updated March 16, 2026
የአካል ጉዳተኞች እና አረጋውያን መብቶች ሁኔታ ዓመታዊ ሪፖርት
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ያዘጋጀው ይህ 3ኛው የአካል ጉዳተኞች እና አረጋውያን መብቶች ሁኔታ ዓመታዊ የዘርፍ ሪፖርት ከሰኔ ወር 2016 ዓ.ም. እስከ ሰኔ ወር 2017 ዓ.ም. ድረስ ያለውን ጊዜ ይሸፍናል። ኢሰመኮ ሐምሌ 28 ቀን 2017 ዓ.ም. 4ኛውን የኢትዮጵያ ዓመታዊ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ሪፖርት ይፋ ያደረገ ሲሆን፣ ይህ የዘርፍ ሪፖርት በተለይም የአካል ጉዳተኞች እና የአረጋውያን ሰብአዊ መብቶችን አስመልክቶ የለያቸውን ቁልፍ እመርታዎች፣ አሳሳቢ ጉዳዮች እና በዘርፉ የሰብአዊ መብቶችን መከበር፣ ጥበቃ እና መስፋፋት ለማሻሻል ሊወሰዱ የሚገባቸውን ምክረ ሐሳቦች አካትቷል።
