- Version
- Download 1
- File Size 884.73 KB
- File Count 1
- Create Date March 16, 2026
- Last Updated March 16, 2026
የማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ መብቶች ሁኔታ ዓመታዊ ሪፖርት
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ መብቶች የሥራ ክፍል የተለያዩ ክትትሎች፣ ምርመራዎች፣ ጥናት እና ምርምሮች፣ የውትወታ ሥራዎች እና የምክክር መድረኮችን የሚያከናውን ሲሆን ይህ ሪፖርትም የተዘጋጀው ከእነዚህ ሥራዎች የተገኙ ግብአቶችን፣ አግባብነት ያላቸው ሰነዶችና ሌሎች የመረጃ/ማስረጃ ምንጮችን መሠረት በማድረግ ነው። ኢሰመኮ በሐምሌ ወር 2017 ዓ.ም. ይፋ ባደረገው 4ኛው የኢትዮጵያ ዓመታዊ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ሪፖርት ላይ የማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ መብቶችን የተመለከቱ ጉዳዮች በአጭሩ የተካተቱ ቢሆንም በ2017 በጀት ዓመት የማኅበራዊ እና የኢኮኖሚያዊ መብቶች ሀገራዊ ሁኔታን ዘርዘር ባለ መልኩ ለማቅረብ ራሱን የቻለ ዓመታዊ የዘርፍ ሪፖርት ተዘጋጅቷል። ይህ የዘርፍ ሪፖርት በዚህ መልኩ ተዘጋጅቶ ሲቀርብ ለ3ኛ ጊዜ ነው።
