የሦስትዮሽ ትብብሩ የመብት ተሟጋቾች ሊደርስባቸው የሚችለውን ጫና እና እንግልት በጋራ ለመከላከል እና ለመቋቋም ትልቅ ሚና ይኖረዋል
የፍትሕ አካላትን የበጀት ውስንነት በመቅረፍ የሚሰጧቸውን አገልግሎቶች ለአካል ጉዳተኞች እና ለአረጋውያን ተደራሽ ለማድረግ የባለድርሻ አካላት በቂ ትኩረት ይፈልጋል
በሥራ ዘርፉ የሚንቀሳቀሱ አስፈጻሚ ተቋማትን በማጠናከር፣ ባለድርሻዎችን አቀናጅቶ እና አስተባብሮ የሚመራ ሥርዓት መዘርጋት አለበት
በማረሚያ ቤቶች እና በፖሊስ ጣቢያዎች የታራሚዎችን እና የተጠርጣሪዎችን አያያዝ ለማሻሻል በኮሚሽኑ የሚሰጡ ምክረ ሐሳቦችን በቁርጠኝነት መፈጸም ያስፈልጋል
National Human Rights Institutions should continue to challenge and advise governments on legal reforms and monitor the implementation of their recommendations
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በተለይ በአፍሪካ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚታሰበውን እና በየዓመቱ እ.ኤ.አ. ሰኔ 30 የሚውለውን የአፍሪካ ሳይንሳዊ ሕዳሴ ቀን (Africa Scientific Renaissance)፣ እንዲሁም የዓመቱ የትምህርት ወቅት መዝጊያን በማስመልከት በተዘጋጀ ማብራሪያ ትምህርት መሠረታዊ የሰብአዊ መብት መሆኑን በማስታወስ፣ በሀገር አቀፍ ደረጃ በግጭት፣ በመፈናቀል፣ በአካል ጉዳት፣ በመሠረተ ልማት ውድመት፣ እንዲሁም በኑሮ ውድነት እና ሌሎች ምክንያቶች ከትምህርት ውጪ ሆነው ለበርካታ ወራት የቆዩ ሕፃናትን በ2016 ዓ.ም. ወደ ትምህርት እንዲመለሱ የማድረጉ ሥራ ከፍተኛ እና የተቀናጀ ትኩረት እንዲሰጠው ጥሪ ያቀርባል።
በፖሊስ ጣቢያዎች ያለውን የተጠርጣሪዎች የሰብአዊ መብቶች አያያዝ ሁኔታ ለማሻሻል የክልሉን ፖሊስ ኮሚሽን ትኩረት እና አፋጣኝ ምላሽ ይፈልጋል
የሚወጡ ሕጎች እና ፖሊሲዎች የአካል ጉዳተኞችን ሰብአዊ መብቶች ያማከሉ እና ልዩ ልዩ ፍላጎቶቻቸውን ያሟሉ መሆናቸውን ማረጋገጥ ያስፈልጋል
የክልል ምክር ቤቶች አስፈጻሚው አካል ላይ የሚያደርጉት ግፊት ኮሚሽኑ ለሚያቀርባቸው ምክረ ሐሳቦች ተፈጻሚነት ወሳኝነት አለው
የማሰቃየት ተግባር ምን ተጽዕኖዎችን ያስከትላል? የማሰቃየትን ተግባርን የሚከለክሉ ዓለም አቀፍ ስምምነቶች የትኞቹ ናቸው? የማሰቃየት ተግባራትን የሚከለክሉ የኢትዮጵያ ሕጎች የትኞቹ ናቸው?