ለችግሩ እልባት የስደተኞች እና ጥገኝነት ጠያቂዎች የምዝገባ አገልግሎት እና የመታወቂያ ሰነድ እድሳት በአፋጣኝ መጀመር አለበት
ሰላማዊ በሆኑ ሃይማኖታዊ ስብስቦች ወቅት የሚወሰድ እርምጃ በተለይም የመንግሥት የጸጥታ አካላትን ከፍተኛ ጥንቃቄ የሚጠይቅ መሆኑን በድጋሚ እናሳስባለን
ጉብኝቱ የኮሚሽኑ ምክረ ሐሳቦች በአስፈጻሚው እንዲተገበሩ የምክር ቤቱን ተጨማሪ ድጋፍ ለማግኘት የሚረዳ ነው
በባሕርይ እና በማኅበራዊ ለውጥ ዙሪያ የሚሠሩ አካላት ብዝኃነትን ማዕከል በማድረግ የአረጋውያንን እና የአካል ጉዳተኞችን ሰብአዊ መብቶች በማስፋፋት ረገድ ጉልህ ሚና አላቸው
ሰብአዊ መብቶች ባህል የሆኑባት ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ በሰብአዊ መብቶች መርሖች እና እሴቶች የታነጸ ትውልድ ማፍራት አስፈላጊ ነው
የአተገባበር ክትትል በተሠራበት በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን እና በሶማሌ ክልል የተለዩ ቦታዎች ዝናብ መዝነቡ የድርቁ አደጋ ማብቂያ ተደርጎ መወሰድ የለበትም
በሀገር ውስጥ በሰዎች የመነገድ ተግባር በተለይም በሴቶችና ሕፃናት መነገድ ሰፊና ውስብስብ ችግር በመሆኑ ልዩ ትኩረት ይሻል
የንግድ ቤቶችን የማፍረስ ሂደት ሕጋዊ ሥርዓትን መከተልና በተለይ በአካል ጉዳተኞች እና አረጋውያን ላይ ሊያስከትል የሚችለውን ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ሥነ-ልቦናዊ ቀውስ ከግንዛቤ በማስገባት መከናወን አለበት
ስልጠናዎቹ ሰብአዊ መብቶችን እና የሰብአዊ መብቶች እሴቶችን መሠረት በማድረግ የሰልጣኞችን ዕውቀት፣ ክህሎት እና አመለካከት ለመገንባት ያለሙ ናቸው
የጤና መብት በተሟላ መልኩ እንዲተገበር የመንግሥት እና የሚመለከታቸው አካላትን ትብብር ይጠይቃል