በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት በተካሄደባቸው አካባቢዎች የተቀበሩና የወዳደቁ ፈንጂዎች በአፋር ክልል 27 ሰዎችን፣ በአማራ ክልል ቁጥራቸው ያልተገለፀ ሰዎችን ለሞት እንዲሁም ለአካል ጉዳት መዳረጋቸውን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን አስታወቀ
ስደተኞች የሚደረግላቸው ጥበቃ እና ድጋፍ በሕግ አግባብ የተመራ እንዲሆን የባለግዴታዎችን ተቀራርቦ መሥራት ይጠይቃል
በማረሚያ ቤት የሚገኙ ታራሚዎችም ሆኑ በፖሊስ ጣቢያዎች ያሉ ተጠርጣሪዎች ኢሰብአዊ ከሆነ አያያዝ ሊጠበቁ ይገባል
የተሐድሶ አገልግሎት ለአካል ጉዳተኞች የሚደረግ እርዳታ ወይም ድጋፍ ሳይሆን ሰብአዊ መብት ነው
የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት፣ ኢትዮጵያን በሚመለከት በቅርቡ ያወጣው የሰብአዊ መብት ሪፖርት፣ ከጣምራ ቡድኑ ሪፖርት ጋራ በአመዛኙ ተመሳሳይ እንደ ኾነ የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ ገለጹ
ሚሊዮን ዜጎቿ ተፈናቅለው የችግርና የሰቀቀን ኑሮ እየገፉ ቢሆንም የእነሱን ጉዳይ ጉዳዬ ብሎ የሚሰራ ተቋም የትኛው ነው ብላችሁ ብትፈልጉ አታገኙም
በአፋር ክልል በጦርነት ምክንያት ለተደጋጋሚ መፈናቀል የተጋለጡ የሁለት ዞን ነዋሪዎች ለከፍተኛ የሰብአዊ ቀውስ መጋለጣቸው ተገለጠ። በተጨማሪም የንግድ እንቅስቃሴው ገደብ በመኖሩ ላልተገባ ኢኮኖሚያዊ ጫና መጋለጣቸውን እና በዘላቂነት እንዲቋቋሙ አለመደረጉን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ባደረገው ክትትል ማረጋገጡን አስታወቀ
መንግሥት በአፋር ክልል በዞን ሁለት፣ በዞን አራት እንዲሁም በሰመራ ከተማ ለሚገኙ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች እና ተመላሾች በቂ፣ ወቅቱን የጠበቀ እና ተደራሽ የሆነ የሰብአዊ ድጋፍ የማቅረብ ኃላፊነቱን በተገቢው መንገድ መወጣት አለበት
ስምምነቱ “የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲው የሲቪክ ማኅበራትን ጨምሮ ከሁሉም ባለድርሻ አካላት በሕዝባዊ ምክክር የሚገኙ ግብአቶችን መሠረት አድርጎ እና መደበኛ ሀገራዊ የፖሊሲ አወጣጥ ሂደቶችን ተከትሎ ሊዘጋጅ እንደሚገባ” ያስቀምጣል
በስደተኞች ሰብአዊ መብቶች ላይ ያለውን ግንዛቤ ማሳደግ፤ በመንግሥት እና በተራድኦ ተቋማት ለስደተኞች የሚቀርቡ የሰብአዊ ድጋፍ እና ሌሎች አገልግሎቶች አካታች፣ ተደራሽ እና ሰብአዊ ክብራቸውን የጠበቁ እንዲሆኑ ይረዳል