
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ/ኮሚሽኑ) ከመስከረም እስከ ታኅሣሥ ወር 2014 ዓ.ም. ድረስ ባሰማራው የሰብአዊ መብቶች ምርመራ ቡድንና ተከታታይ የምርመራ ስልቶች በአፋርና አማራ ክልሎች ተስፋፍቶ በቆየው ጦርነት የተከሰቱ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶችን መርምሯል፡፡ ⬇️ ሙሉ ሪፖርቱ ያለ አባሪዎቹ ⬇️ የሪፖርቱ አባሪዎች ⬇️ የሪፖርቱ አንኳር ጉዳዮች ⬇️ Executive Summary

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን እና የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር ጽሕፈት ቤት፣ በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ትግራይ ክልል ውስጥ በተፈጠረው ግጭት ወቅት በሁሉም የግጭቱ ተሳታፊ አካላት ተፈጽመዋል የተባሉትን የዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች፣ የሰብአዊነት እና የስደተኞች ሕግጋት ጥሰቶች በተመለከተ በጋራ ያካሄዱት የምርመራ ሪፖርት የእንግሊዝኛውን ሪፖርት ያንብቡ



የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ለሀገራዊ ምርጫ 2013 ዓ.ም. ባለ6 ነጥብ የሰብአዊ መብቶች አጀንዳ ይፋ በማድረግና ለሰብአዊ መብቶች ትኩረት እንዲሰጥ ከመወትወት በተጨማሪ፤ በቅድመ ምርጫውና በምርጫው ቀን የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ክትትል ሲያከናውን ቆይቷል።

የሰብአዊ መብቶች ምርጫ ክትትል ቡድኖች በሚሰማሩባቸው ስፍራዎች በምርጫው እለት እና ከምርጫው በኋላ ባሉት ቀናት በምርጫ ጣቢያዎችም በመገኘት ምልከታ ያደርጋሉ