ኢሰመኮ በተለይ በአዲስ አበባ ከተማ፣ በኦሮሚያና በአማራ ክልሎች ከደረሱት አቤቱታዎችና ጥቆማዎች በመነሳት ሲያደርግ በነበረው ክትትል መሠረት በርካታ የአስገድዶ መሰወርን ድርጊት የሚያቋቁሙ ድርጊቶች መከሰታቸውን አረጋግጫለሁ ብሏል
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በኢትዮጵያ ውስጥ የተለያዩ አካባቢዎች እየጨመረ የመጣውን የአስገድዶ መሰወር እና ተይዘው የሚገኙበት ሁኔታ ሳይታወቅ በእስር ላይ የሚገኙ ሰዎችን ጉዳይ እየተከታተለ መሆኑን ገልጿል
የአስገድዶ መሰወር ወንጀልን ውጤታማ በሆነ መንገድ ለመከላከል ይረዳ ዘንድ፤ ሁሉንም ሰዎች ከአስገድዶ መሰወር ለመጠበቅ የተደረገውን ዓለም አቀፍ ስምምነት (International Convention for the Protection of All Persons from Enforced Disappearance) ኢትዮጵያ በአስቸኳይ ተቀብላ ልታጸድቅ ይገባል
በአማራ ክልል የሀገር መከላከያ እና በአካባቢው ታጣቂዎች በከባድ መሳሪያ የታገዘ ግጭት ውስጥ መግባታቸውን ኢሰመኮ ገለጸ
The Ethiopian Human Rights Commission (EHRC) said it is “closely monitoring” the ongoing “law enforcement campaign” in some areas of the Amhara regional state and its implications and effects on human rights
በአማራ ክልል በሚገኙ የተለያዩ አካባቢዎች ውስጥ በመከላከያ ሠራዊት እና በታጣቂዎች መካከል ግጭት መኖሩን እና በሰው ሕይወት ላይ ጉዳት መድረሱን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አስታወቀ
ሁሉም የሚመለከታቸው ወገኖች ችግሩን በውይይት እንዲፈቱ፣ ግጭቱን ከሚያባብሱ ድርጊቶችና ንግግሮች እንዲቆጠቡ እና ስለደረሰው ጉዳት አስፈላጊውን ምርመራ በማድረግ ተጠያቂነት እንዲረጋገጥ ያስፈልጋል
ኢሰመኮ ከመደበኛው የክትትል እና ምርመራ ሥራው ጎን ለጎን ምክረ ሐሳቦችን በመስጠት የተፈጠረው ችግር በውይይት እንዲፈታ ጥረት እያደረገ ይገኛል
ኢሰመኮ የፀጥታ አካላት ያልተመጣጠነ ኃይል ከመጠቀም እንዲቆጠቡ፣ ሁሉም ሰው ሃሳቡን በሕጋዊ እና በሰላማዊ መንገድ እንዲገልጽ ጥሪ ያቀረበ ሲሆን፣ መንግሥት ለደረሰው ጉዳት አስፈላጊውን ምርመራ በማድረግ ተጠያቂነት እንዲሰፍንም ጠይቋል
የኢትዮጵያ መንግሥት፣ የክልሎች ልዩ ኃይሎችን መልሶ ለማደራጀት የጀመረው ፕሮግራም፣ ሰብአዊ መብቶችን አደጋ ላይ በማይጥል አሠራር እንዲተገበር የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን አሳሰበ