የብሔራዊ ምርመራ/ግልጽ ምርመራ በሕዝብ ፊት የሚካሄዱ የአቤቱታ መቀበያ መድረኮቹን ተከትሎ ግኝቶችን እና ምክረ ሐሳቦችን የያዘ ሪፖርት ይፋ የሚደረግ ይሆናል
የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት፣ ኢትዮጵያን በሚመለከት በቅርቡ ያወጣው የሰብአዊ መብት ሪፖርት፣ ከጣምራ ቡድኑ ሪፖርት ጋራ በአመዛኙ ተመሳሳይ እንደ ኾነ የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ ገለጹ
በኮሚሽኑ የሴቶችና ህጻናት መብቶች ኮሚሽነር መስከረም ገስጥ በመግለጫው እንዳሉት ከህግ አግባብ ውጭ የተፈጸሙ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ላይ በማተኮር አቤቱታዎች የሚደመጡ ይሆናል
ነጻነታቸውን ከሕግ አግባብ ውጭ እና በዘፈቀደ ተነፍገናል የሚሉ ሰዎችን አቤቱታ መቀበያ መድረክ በባሕርዳር ከተማ ሊያካሂድ መኾኑን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ገልጿል
ስምምነቱ “የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲው የሲቪክ ማኅበራትን ጨምሮ ከሁሉም ባለድርሻ አካላት በሕዝባዊ ምክክር የሚገኙ ግብአቶችን መሠረት አድርጎ እና መደበኛ ሀገራዊ የፖሊሲ አወጣጥ ሂደቶችን ተከትሎ ሊዘጋጅ እንደሚገባ” ያስቀምጣል
«ታጣቂዎቹ ጥቃቱን ባደረሱበት ከተማ ከማኅበረሰቡ ጋር ተቀላቅለው የሚኖሩ ተፈናቃዮችን ቤትለቤት እየዞሩ በተለይ የአማራ ብሔር ተወላጆችን ለይተው ገድለዋል» በማለት የምርመራ ግኝቱ ጠቁሟል
አካል ጉዳተኛ ተማሪዎች በትምህርት ተቋማት የሚያጋጥማቸውን የከባቢያዊ፣ የአመለካከት፣ የተግባቦት እና ተያያዥ ተቋማዊ ተግዳሮቶችን ለመቅረፍ የሁሉንም ባለድርሻ አካላት ርብርብ ይጠይቃል
በስደተኞች ሰብአዊ መብቶች ላይ ያለውን ግንዛቤ ማሳደግ፤ በመንግሥት እና በተራድኦ ተቋማት ለስደተኞች የሚቀርቡ የሰብአዊ ድጋፍ እና ሌሎች አገልግሎቶች አካታች፣ ተደራሽ እና ሰብአዊ ክብራቸውን የጠበቁ እንዲሆኑ ይረዳል
ኢሰመኮ በሁለት ዓመቱ የጦርነት ወቅት የተፈጸሙ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን የሚመለከት ተጨማሪ ምርመራ አያደርግም ያሉት ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር)፣ ይህ የሚከናወነው የሽግግር ወቅት ፍትህን በሚመራው አካል እንደሆነም ጠቅሰዋል
The Human Rights Film Festival is said to return for the third round at the same time next year