በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል፣ መተከል ዞን ግልገል በለስ ከተማ፣ ባለፈው ሳምንት አርብ ሰኔ 30 በታጣቂዎች በተሰነዘረ ጥቃት፤ ሶስት የአካባቢ ሚሊሺያዎችን ጨምሮ ስምንት ሰዎች መገደላቸውን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አስታወቀ
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ዶክተር ዳንኤል በቀለ አጠቃላይ የደረሰውን ጉዳት ለማጣራት ምርመራ እያደረግን ነው፤ ለጊዜው ግን ንጹሃን ዜጎች እና የመከላከያ ሰራዊት አባላት በታጣቂው መገደላቸውን አረጋግጠናል ብለዋል
የመተከል ዞን ሰላም እና ደኅንነት ዘላቂ በሆነ መልኩ እንዲመለስ የተጀመሩ የሰላም ሂደቶችን አፈጻጸምና ውጤት መከታተል ይገባል
የፍትሕ አካላትን የበጀት ውስንነት በመቅረፍ የሚሰጧቸውን አገልግሎቶች ለአካል ጉዳተኞች እና ለአረጋውያን ተደራሽ ለማድረግ የባለድርሻ አካላት በቂ ትኩረት ይፈልጋል
መንግሥት በታራሚዎች ላይ የሚፈጸም ድብደባን በሕገ-መንግሥቱ መሠረት ሊያርም እንደሚገባ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አሳሰበ
አማራጭ የቅጣት ፖሊሲ እና የግጭት መፍቻ ዘዴዎችን በመጠቀም በፍትሕ ሥርዓቱ በተለይም በማረሚያ ቤቶች የሚስተዋለውን ጫና መቀነስ ይቻላል
በተጠርጣሪዎች ላይ ድብደባና ኢሰብአዊ ድርጊቶችን የሚፈጽሙ የጸጥታ አካላት ላይ ሕጋዊ እርምጃ መውሰድና ተጠያቂነትን ማረጋገጥ ያስፈልጋል
ሰብአዊ ክብር፣ እኩልነት፣ አድሎ አለመፈጸም፣ ፍትሐዊነት እና አካታችነትን የመሳሰሉ መሠረታዊ የሆኑ የሰብአዊ መብቶች እሴቶች፤ የአካል ጉዳተኞች ማኅበራት ለአባሎቻቸው እና ለተጠቃሚዎች በሚሰጡት አገልግሎት ሊጠብቋቸው የሚገቡ እሴቶች ናቸው
በስደተኞች ሰብአዊ መብቶች ላይ ያለውን ግንዛቤ ማሳደግ፤ በመንግሥት እና በተራድኦ ተቋማት ለስደተኞች የሚቀርቡ የሰብአዊ ድጋፍ እና ሌሎች አገልግሎቶች አካታች፣ ተደራሽ እና ሰብአዊ ክብራቸውን የጠበቁ እንዲሆኑ ይረዳል
በፖሊስ ጣቢያዎች በተደረገው ክትትል የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን የሰጣቸውን ምክረ-ሃሳቦች ተቀብሎ በመፈጸም ረገድ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ መሻሻሎች መስተዋላቸው አበረታች ነው