የምግብ ድጋፍ አቅርቦት ወቅቱን የጠበቀ፣ በቂ፣ ተደራሽ እና የሕፃናትን፣ ሴቶችን፣ አካል ጉዳተኞችንና አረጋውያንን ልዩ ፍላጎት ያገናዘበ ሊሆን ይገባል
በጥቃቱ ስምንት ሰዎች ሲሞቱ 16 ሰዎች ደግኖ ቆስለዋል ተብሏል
ጥቃቱ የተፈጸመው በግልገል በለስ ከተማ፣ በተለምዶ “ቻይና ካምፕ” ተብሎ በሚጠራ ሰፈር ከቀኑ 11፡30 ሰዓት ጀምሮ ሲሆን፣ 3 የአካባቢውን ሚሊሻ አባላት ጨምሮ 8 ነዋሪዎች መገደላቸውን፣ በ16 ሲቪል ሰዎች ላይ ደግሞ ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶ የሕክምና እርዳታ እያገኙ መሆኑን፣ በርካታ ሌሎች ነዋሪዎች ቻይና ካምፕን ለቀው ወደ ሌላ ሰፈር መሸሻቸው ታውቋል
በመተከል ዞን ከሰሞኑ የተፈጠረው ጥቃትም የዚህ ማሳያ ነው ያለው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን መንግስት የሰላም ሂደት አፈፃፀሙን እንዲከውን አሳስቧል
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል፣ መተከል ዞን ግልገል በለስ ከተማ፣ ባለፈው ሳምንት አርብ ሰኔ 30 በታጣቂዎች በተሰነዘረ ጥቃት፤ ሶስት የአካባቢ ሚሊሺያዎችን ጨምሮ ስምንት ሰዎች መገደላቸውን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አስታወቀ
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ዶክተር ዳንኤል በቀለ አጠቃላይ የደረሰውን ጉዳት ለማጣራት ምርመራ እያደረግን ነው፤ ለጊዜው ግን ንጹሃን ዜጎች እና የመከላከያ ሰራዊት አባላት በታጣቂው መገደላቸውን አረጋግጠናል ብለዋል
የመተከል ዞን ሰላም እና ደኅንነት ዘላቂ በሆነ መልኩ እንዲመለስ የተጀመሩ የሰላም ሂደቶችን አፈጻጸምና ውጤት መከታተል ይገባል
የፍትሕ አካላትን የበጀት ውስንነት በመቅረፍ የሚሰጧቸውን አገልግሎቶች ለአካል ጉዳተኞች እና ለአረጋውያን ተደራሽ ለማድረግ የባለድርሻ አካላት በቂ ትኩረት ይፈልጋል
መንግሥት በታራሚዎች ላይ የሚፈጸም ድብደባን በሕገ-መንግሥቱ መሠረት ሊያርም እንደሚገባ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አሳሰበ
አማራጭ የቅጣት ፖሊሲ እና የግጭት መፍቻ ዘዴዎችን በመጠቀም በፍትሕ ሥርዓቱ በተለይም በማረሚያ ቤቶች የሚስተዋለውን ጫና መቀነስ ይቻላል