የሴት ልጅ ግርዛት በሴቶች እና በሴት ሕፃናት ላይ የሚያስከትለው ተደራራቢ የመብቶች ጥሰት እና ጉዳት አሳሳቢ በመሆኑ የመንግሥትን እና የሌሎች ባለድርሻ አካላትን ትኩረት ይሻል
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በማእከላዊ ኢትዮጵያ እና በደቡብ ኢትዮጵያ ክልሎች በተለይም ከአዳዲስ የክልል አደረጃጀቶችና መዋቅሮች መቋቋም ወይም ተያያዥ ውሳኔዎች ጋር በተያያዘ የሚነሱ የደመወዝ መዘግየትን እና ያለመከፈልን የተመለከቱ አቤቱታዎችን እና ጥቆማዎችን መነሻ በማድረግ የሰብአዊ መብቶች ምርመራ በማከናወን ታኅሣሥ 13 ቀን 2016 ዓ.ም. ሪፖርት (ከዚህ በኋላ “ዋናው የምርመራ ሪፖርት”) ይፋ ማድረጉ ይታወቃል። በዚሁ መሠረት፣ ከ2012 ዓ.ም....
የክልሉን የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ለማሻሻል በጎ ጅምሮችን ማጠናከር እንዲሁም በክትትል እና ምርመራ ግኝቶች መሠረት የቀረቡ ምክረ ሐሳቦችን መተግበር ያስፈልጋል
ኢሰመኮ ይህን ያለው ሰኔ 16/2016 ዓ.ም በ4 ክልሎች የተካሄደውን የ6ኛ ዙር ቀሪና ድጋሚ ምርጫ የሰብአዊ መብቶችን ክትትል በመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርቱ ነው
ሰኔ 21፣ 2016 (አራዳ ኤፍ ኤም) የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ሰኔ 16 ቀን በተካሄደው የ6ኛው የቀሪ እና ድጋሚ ምርጫ ወቅት የነበሩ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታን ክትትል የያዘ የመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርት ይፋ አድርጓል
ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በዕለቱ ምርጫ እንዳይካሄድ ከወሰነባቸው አካባቢዎች በስተቀር ምርጫው በአብዛኛው ሰላማዊ እና የሰብአዊ መብቶች መርሖችን ባከበረ መልኩ ተጠናቋል
በሴቶች ላይ የሚፈጸም ግርዛትና ተደጋጋሚ ግርዛትን ለማስቆም ሁሉም ባለድርሻ አካላት ማኅበረሰቡን ለማስተማርና ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ በጋራ መሥራት ይጠበቅባቸዋል
በጤናና በትምህርት፣ እንዲሁም በሌሎችም ማኅበራዊ አገልግሎት ሰጪ የመንግሥት ተቋማት ላይ ቅኝት በማድረግ ምርመራ ማድረጉን የኮሚሽኑ የማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ መብቶች ሥራ ክፍል ኃላፊ ዶ/ር ብራይትማን ገብረሚካኤል ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል፣ በጉራጌ ዞን እና በቀቤና ልዩ ወረዳ መካከል የነበረውን አለመግባባት ተከትሎ ጥቅምት 2 ቀን 2016 ዓ.ም. ጀምሮ የተከሰተውን የጸጥታ መደፍረስና ያስከተለውን ጉዳት ከአካባቢው ነዋሪዎች በቀረበለት አቤቱታ መነሻነት ከጥቅምት 20 እስከ 25 ቀን 2016 ዓ.ም. በቦታው በመገኘት ጭምር ምርመራ ማከናወኑን አስታውቋል
በወልቂጤ ከተማ ጥቅምት 2 ቀን 2016 ዓ.ም. ለተከሰተው ሁከት እና የደረሰውን ጉዳት በተመለከተ ተገቢውን ማጣራት በማድረግ ተጠያቂነት ማረጋገጥ፣ እንዲሁም ለተፈናቃዮች እና ተጎጂዎች አስፈላጊው ድጋፍ እና ካሳ ሊሰጣቸው ይገባል