በአዲስ መልኩ በሚዋቀሩ አካባቢዎች የሚነሱ የደመወዝ እና ተያያዥ ጥያቄዎች አፋጣኝ መፍትሔ መስጠት በጤና እና በትምህርት መብት እንዲሁም በአካባቢዎቹ አጠቃላይ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ላይ ያሉ ሥጋቶችን ይቀርፋል
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የመዋቅር እና የአስተዳደር ጥያቄዎች ለሰላም እጦት ምክንያት መሆናቸው እንዳሳሰበው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ዐስታወቀ ፡፡ በክልሉ በጉራጌ ዞን እና በቀቤና ልዩ ወረዳ መካከል የነበረው አለመግባባት በአካባቢው የፀጥታ መደፍረስን ማስከተሉን ኮሚሽኑ ዛሬ ባወጣው የምርመራ ሪፖርቱ ዐስታውቋል
በወልቂጤ ከተማ ለውሃ አቅርቦት ጥያቄ አደባባይ በወጡ ነዋሪዎች ላይ ያልተመጣጠነ፤ ኃይል ተጠቅሞ ጥቃት በማድረስ ሕይወት እንዲጠፋና የአካል ጉዳት እንዲደርስ ያደረጉ የመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች ተጠያቂ እንዲሆኑ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አሳሰበ
ተመሳሳይ ዓይነት የመብት ጥሰቶች እንዳይፈጸሙ ለጸጥታ ኃይሎች ግልጽ አመራር ማስተላለፍ ያስፈልጋል