ለማንኛውም ዓላማ በሰው የመነገድ ተግባር የተከለከለ ነው
Trafficking in human beings for whatever purpose is prohibited
በሰብአዊ መብቶች ላይ በጋራ መምከር እና አጋርነትን ማጠናከር ለሰብአዊ መብቶች መስፋፋት፣ መከበር እና ጥበቃ ጉልህ ሚና አለው
ኮሚሽነሮቹ በሰጡት አመራር የኢሰመኮን ሥራ በማጠናከር፣ ተደራሽነቱን በማስፋት እና በሕዝብ እንዲሁም በዓለም አቀፍ አጋሮች ዘንድ መተማመንን በማሳደግ ረገድ የሚጠበቅባቸውን ሚና አበርክተዋል
ማንኛውም አካል ጉዳተኛ ሰው ዘርን፣ ጎሳን፣ የቆዳ ቀለምን፣ ጾታን፣ ቋንቋን፣ ሃይማኖትን፣ ፖለቲካን ወይም በሌላ ዐይነት አመለካከት፣ በብሔራዊ ወይም ማኅበራዊ መሠረትን፣ ሃብትን፣ ትውልድን ወይም ሌላ ሁኔታን ጨምሮ በማንኛውም ምክንያት ማንኛውም ዐይነት ልዩነት ሳይደረግበት በዚህ ፕሮቶኮል ውስጥ ዕውቅናና ዋስትና የተሰጣቸው መብቶች እና ነጻነቶችን የማግኘት እና የመጠቀም መብት አለው
ጉዳትን መሠረት ያደረገ ተመጣጣኝ ማመቻቸት በማቅረብ አካል ጉዳተኛ የመንግሥት ሠራተኞችን ሰብአዊ መብቶች ማረጋገጥ ይገባል
በሰብአዊ መብቶችና በሲቪክ ምኅዳሩ ዙሪያ በሀገር አቀፍ ደረጃ ለሚታዩ ተግዳሮቶች መፍትሔ ለማምጣት የሚመለከታቸው አካላት በአጋርነት ሊሠሩ ይገባል
የስደተኞች መብቶች ጥበቃን ለማጎልበት የስደተኛ ማኅበረሰብ ተወካዮችን እና ማኅበራትን በማጠናከር አሳታፊ የሆኑ ፖሊሲዎች፣ ፕሮግራሞች እና አሠራሮችን መተግበር ያስፈልጋል
በውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት እና የሥራ ፍልሰት አስተዳደርን በማጎልበት የሚያጋጥሙ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶችን ለማሻሻል የሀገራትን መልካም ተሞክሮዎች መውሰድ እና የባለድርሻ አካላት ትብብርን ማጠናከር ይሻል
ከዴሞክራሲ ተቋማት ጋር እየተደረገ ባለው የጋራ ምክክር መድረክ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ)፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እና የኢትዮጵያ ሕዝብ እምባ ጠባቂ ተቋም የሪፎርም ዕቅድ አፈጻጸማቸውን አቅርበዋል