በተለይም ግጭት ባለባቸው በኦሮሚያ፣ አማራ እና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች በታጣቂዎች በሚፈጸም ጥቃት እና መንግሥት ያንን ለመከላከል አልያም ለፍትሕ ለማቅረብ በሚደርገው እንቅስቃሴ ውስጥ ንፁሐን እየሞቱ እና እየተጎዱ መሆኑን መንግሥታዊው የሰብአዊ መብቶች ተቆርቋሪው ኢሰመኮ ተናግሯል
በ2016 ዓ.ም. በበርካታ የኢትዮጵያ አከባቢዎች በተለምዶ ወቅታዊ ሁኔታ በሚል ምክንያቶች ሳቢያ ሰዎች ለዘፈቀደ እስር እንዲሁም ለአስገድዶ መሰወር የተዳረጉበት በርካታ ክስተቶች መመዝገቡን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን አስታወቀ
ኮሚሽኑ ከሰኔ ወር 2015 ዓ.ም. እስከ ሰኔ ወር 2016 ዓ.ም. ያለውን ጊዜ የሚሸፍነው 3ኛው የኢትዮጵያ ዓመታዊ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ሪፖርት ይፋ አድርጓል
ዓለም አቀፉ የአካል ጉዳተኞች መብቶች ስምምነት በሀገራዊ ቋንቋዎች መተርጎም የስምምነቱን ተደራሽነት በማስፋት ለአካል ጉዳተኞች ሰብአዊ መብቶች መከበር አስተዋጽዖ አለው
EHRC reiterates its call for the implementation of legal, political, administrative and social measures to prevent and respond to internal trafficking in women and children
የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች በቂ እና ወቅቱን የጠበቀ የምግብ ድጋፍ እየቀረበላቸው ባለመሆኑ ለረሀብ አደጋ እየተጋለጡ ናቸው
Trafficking in human beings for whatever purpose is prohibited
ለማንኛውም ዓላማ በሰው የመነገድ ተግባር የተከለከለ ነው
የሰንዳይ የአደጋ ሥጋት ቅነሳ ማዕቀፍ (እ.ኤ.አ. 2015-2030) በ187 አባል ሀገራት በ3ኛው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአደጋ ሥጋት ቅነሳ ጉበኤ እ.ኤ.አ. መጋቢት 18 ቀን በ2015 ጸድቋል። ይህ ማዕቀፍ መንግሥታት በቀዳሚነት የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ላይ ማተኮር እንዳለባቸው በመግለጽ፣ ኃላፊነቱ በዋነኛነት መንግሥት ላይ የሚወድቅ ቢሆንም ሁሉም ማኅበረሰብ እና ሌሎች ባለድርሻ አካላትም የአደጋ ሥጋት ቅነሳ ሥራዎች ላይ መሳተፍ እንዳለባቸው ያስረዳል
የሰብአዊ መብቶች ምርመራ እና የወንጀል ምርመራ ሕጋዊና ተቋማዊ ማዕቀፎች ምንድን ናቸው? የሁለቱ የምርመራ ዐይነቶች ዓላማዎችና ግቦች ምንድን ናቸው? በሁለቱ የምርመራ ዘርፎች መካከል ያለው የማስረጃ ምዘና ስልት ልዩነት ምን ይመስላል? ሁለቱ የምርመራ ዘርፎች የሰብአዊ መብቶችን ጥበቃ ለማሻሻል በምን መንገድ ሊደጋገፉ ይችላሉ?