የህወሓት ታጣቂዎች በተለያዩ የአማራና የአፋር ክልሎች አካባቢዎች ውስጥ “ከባድ ሊባሉ የሚችሉ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶችን ስለመፈፀማቸው አቤቱታዎች እንደደረሱት” የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን አስታውቋል።
የተባበሩት መንግሥታት ባጸደቀው "የፓሪስ መርኆዎች" በተሰኘው መለኪያ መሰረት የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በተአማኒነቱ ወደ ከፍተኛው ደረጃው 'ኤ' እንዲገባ ዓለም አቀፉ የብሔራዊ የሰብአዊ መብቶች ጥምረት መወሰኑ ይፋ ተደረገ።
ከጠንካራ የግምገማ ሂደት በኋላ የሚሰጠውን የዓለም አቀፉ የብሔራዊ ሰብአዊ መብቶች ተቋማት ጥምረት (Global Alliance of National Human Rights Institutions (GANHRI)) የደረጃ “A” (አንደኛ ደረጃ) እውቅና ማግኘቱ ኮሚሽኑ የፓሪስ መርሆችን ሙሉ በሙሉ ማሟላቱን የሚያሳይ ነው።
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ፊልም ፌስቲቫል በኅዳር 28 ቀን 2014 ዓ.ም. በአዳማ ኦሊያድ ሲኒማ፣ በኅዳር 29 ቀን 2014 ዓ.ም. ደግሞ በሀዋሳ ከተማ ሌዊ ሲኒማ በመጨረሻም በታኅሣሥ 1 ቀን 2014 ዓ.ም. በአዲስ አበባ በጋርደን ግሩቭ ዎክ መናፈሻ ይካሄዳል
ኮሚሽኑ ይህንኑ ቀን ለማሰብ ባሰራጨው በዚህ አጭር ቪድዮ የአካል ጉዳተኞችን እኩል ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በመንግስትም ሆነ በሌሎች አካላት ከወዲሁ መወሰድ ስለሚችሉ እርምጃዎች ግንዛቤ ይሰጣል፣ ውትወታ ያደርጋል
ኢሰመኮ በተለይም ከእ.ኤ.አ. ከኅዳር 11 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ ለሚታሰቡ የተለያዩ ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ቀናት #ጤናማቃላት ወይም #KeepWordSafe የሚል የማኅበራዊ ድረ ገጽ እንቅስቃሴ “ሃሽታግ” እና ታስበው የሚውሉትን ዓለም አቀፍ ቀናት ማሳወቁ ይታወሳል።
ለባለፉት በርካታ ወራት ሰፊ አካታች ሂደት ሲዘጋጅ የቆየው ይህ የስትራቴጂ እቅድ ኮሚሽኑ ለቀጣይ አምስት ዓመታት ሊሰሩና ትኩረት ሊሰጣቸው ይገባል ብሎ የለያቸው ቁልፍ የውጤት መስኮችንና ዋና ዋና ተግባራትን አካቷል።
የሰብአዊ መብት ተሟጋች ዶ/ር ዳንኤል በቀለ ትናንት በርሊን ብራንድቡርግ፤ የ2021 የጀርመን አፍሪቃ ሽልማት ተቀበሉ።
በጦርነቱ ወቅት ትግራይ ውስጥ “ተፈጽመዋል” የተባሉት የሰብዓዊ መብት ዓለም አቀፍ ድንጋጌዎችን፣ የስብዕና እና የስደተኛ ሕግጋት መጣስ ሲያጣራ የቆየው ጥምር መርማሪ ቡድን ባወጣው የግኝቱ ሪፖርት የጦር ወንጀሎች እና በስብዕና ላይ የተፈጸሙ ሊባሉ የሚችሉ ወንጀሎች በሁሉም ወገኖች ስለመፈጸማቸው አሳማኝ መሰረቶች አሉ ብሏል።
ኢሰመኮ በማቋቋሚያ አዋጁ በተሰጠው ሥልጣን መሰረት በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁም ወቅት ሰብአዊ መብቶችን የሚከታተል መሆኑንና የሚመለከታቸው አካላት በሙሉ ለኮሚሽኑ የክትትል ተግባራት ትብብር የማድረግ ግዴታ እንዳለባቸው ለማስታወስ ይወዳል