ለባለፉት በርካታ ወራት ሰፊ አካታች ሂደት ሲዘጋጅ የቆየው ይህ የስትራቴጂ እቅድ ኮሚሽኑ ለቀጣይ አምስት ዓመታት ሊሰሩና ትኩረት ሊሰጣቸው ይገባል ብሎ የለያቸው ቁልፍ የውጤት መስኮችንና ዋና ዋና ተግባራትን አካቷል።
የሰብአዊ መብት ተሟጋች ዶ/ር ዳንኤል በቀለ ትናንት በርሊን ብራንድቡርግ፤ የ2021 የጀርመን አፍሪቃ ሽልማት ተቀበሉ።
በጦርነቱ ወቅት ትግራይ ውስጥ “ተፈጽመዋል” የተባሉት የሰብዓዊ መብት ዓለም አቀፍ ድንጋጌዎችን፣ የስብዕና እና የስደተኛ ሕግጋት መጣስ ሲያጣራ የቆየው ጥምር መርማሪ ቡድን ባወጣው የግኝቱ ሪፖርት የጦር ወንጀሎች እና በስብዕና ላይ የተፈጸሙ ሊባሉ የሚችሉ ወንጀሎች በሁሉም ወገኖች ስለመፈጸማቸው አሳማኝ መሰረቶች አሉ ብሏል።
ኢሰመኮ በማቋቋሚያ አዋጁ በተሰጠው ሥልጣን መሰረት በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁም ወቅት ሰብአዊ መብቶችን የሚከታተል መሆኑንና የሚመለከታቸው አካላት በሙሉ ለኮሚሽኑ የክትትል ተግባራት ትብብር የማድረግ ግዴታ እንዳለባቸው ለማስታወስ ይወዳል
ጊዳ ኪራሙ ወረዳን ጨምሮ በተለያዩ የምስራቅ ወለጋ ወረዳዎች ውስጥ የሚገኙ ነዋሪዎች በአስጊ ሁኔታ ይገኛሉ
ረቂቅ የወንጀል ሥነ ሥርዓትና የማስረጃ ሕጉ የእስረኛ እናቶችን እና ብቸኛ አሳዳጊዎች ልጆች ሰብአዊ መብቶች ጥበቃ በተመለከተ ሊያካትታቸው የሚገባቸው ነጥቦች ላይ ከኢሰመኮ የተዘጋጀ አጭር ማብራሪያ