የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽንና የተባበሩት መንግሥታት ባለፈው ዓመት ባደረጉት ጣምራ ምርመራበትግራይ ክልል ውስጥ በነበረው ጦርነት በሰብዓዊነት ላይ የተፈፀመ እና የጦር ወንጀል ሊባሉ የሚችሉ የወንጀል ዓይነቶች መፈፀማቸውን የሚያመለክቱ ማስረጃዎች መገኘታቸውን አመልክተው ነበር
ከሰኔ 7 እስከ ሰኔ 9 ቀን 2014 ዓ.ም. የተፈጸሙ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች ተጎጂዎች እና የተጎጂ ቤተሰቦች...
ትናንት መስከረም 25/2015 በቡድን ሆነው የመጡ ሰዎች ወደ ኢሰመኮ ጋምቤላ ጽሕፈት ቤት በመግባት የተለያዩ የጥፋት ድርጊቶችን መፈጸማቸውንና በኢሰመኮ ባልደረቦች ላይ ዛቻ እና ማስፈራሪያ ማድረሳቸውን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አስታወቀ
ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ ድርጊቱ በክልሉ የሰብአዊ መብቶች አያያዝ ላይ ከፍተኛ አሉታዊ ምልከታ የሚጥል ነው ብለዋል
ኢሰመኮ ይህን የገለጸው በወቅቱ በጋምቤላ ከተማ የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን አስመልክቶ ዛሬ ረቡዕ መስከረም 18፤ 2014 ይፋ ባደረገው የምርመራ ሪፖርት ነው። ኮሚሽኑ በዚሁ ሪፖርቱ፤ ሰኔ 7፤ 2014 በጋምቤላ ከተማ የተደረገውን ውጊያ ተከትሎ፤ ኢሰመኮ አንድ ወር ለሚጠጋ ጊዜ ምርመራ ሲያደርግ እንደነበር አስታውቋል
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በጋምቤላ ከተማ ሰኔ 7 ቀን 2014 ዓ.ም. በክልሉ የጸጥታ ኃይሎች፣ በኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት (በተለምዶ ኦነግ ሸኔ) እና በጋምቤላ ነጻነት ግንባር (ጋነግ) መካከል የተደረገው ውጊያን ተከትሎ ከሰኔ 7 እስከ 9 ቀን 2014 ዓ.ም. በክልሉ የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች እንዲሁም ታጣቂ ኃይሎች በተወሰዱ እርምጃዎች በሲቪል ሰዎች ላይ የተፈጸሙ ግድያዎችን፣ የአካል ጉዳቶችን፣ የንብረት ጉዳት...
በጋምቤላ ከተማ ሰኔ 07/2014 ዓ.ም በክልሉ የፀጥታ ኃይሎች፣ በኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት እና በጋምቤላ ነጻነት ግንባር የተደረገውን ውጊያ ተከትሎ ቢያንስ 50 ሰላማዊ ሰዎች በፀጥታ ኃይሎች መገደላቸውን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሸን (ኢሰመኮ) አስታወቀ
በድርጊቱ የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ታጣቂ ቡድን፣ የጋምቤላ ነጻነት ግንባር ታጣቂ ቡድን፣ የጋምቤላ ክልል ልዩ ኃይሎች፣ ፖሊሶች፣ ሚሊሻዎች እና ተባባሪ ወጣቶች ተሳትፈዋል፤ ድርጊቱን ሲመሩ እና ሲያስፈጽሙ የነበሩ ኃላፊዎችም ነበሩ
የቀረቡ ምክረ ሃሳቦችን ለማስፈጸም የሁሉም ባለድርሻ አካላት ትብብር አስፈላጊ ነው
የፀጥታ ኃይሎች ሕይወት ሊያጠፋ ከሚችል ተመጣጣኝ ያልሆነ የኃይል እርምጃ መቆጠብ እና በፀጥታ ኃይሎች የተወሰዱ ሕገ ወጥ ተግባራት ላይ በአስቸኳይ ማጣራት ተደርጎ ተጠያቂነት ሊረጋገጥ ይገባል