በሲቪል ሰዎች ላይ ለደረሰው ግድያ፣ ጉዳት እና መፈናቀል ተጠያቂነት ሊረጋገጥ አንደሚገባ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አሳሰበ
በሲቪል ሰዎች ላይ ለደረሰው ግድያ፣ ጉዳት እና መፈናቀል ተጠያቂነት ሊረጋገጥ፣ የመንግሥት ፀጥታ ኃይሎች ስምሪትን የተመለከቱ እርምጃዎች የሰዎች ደኅንነት ላይ ስጋት በማያሳድር መልኩ ሊሆን ይገባል
የኦሮምያ ክልል ማረሚያ ቤቶች ውስጥ ከሕግ አግባብ ውጭ የሚፈፀሙ እሥራቶችና የተያዙ ሰዎችን መብቶች የሚጥሱ አሠራሮችን መመልከቱን የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን አስታውቋል
የፖሊስ እና የማረሚያ ቤቶች ሥራ በሰብአዊ መብቶች መርሆዎች የተመራ ሊሆን ይገባል
ኮሚሽኑ በ126 ፖሊስ ጣቢያዎች ባደረገው ክትትል፣ ታሳሪዎች የታሰሩበትን ምክንያት አለመንገር፣ ሰዎችን በአስተዳደር አካላት ትዕዛዝ ብቻ ማሰር፣ ዋስትና የተፈቀደላቸውን ሰዎች አስሮ ማቆየት፣ ባልተያዙ የወንጀል ተጠርጣሪዎች ምትክ ቤተሰቦቻቸውን ማሰር፣ ተጠርጣሪዎች የተጠረጠሩበትን ወንጀል እንዲያምኑ መደብደብና ምግብ፣ መጠጥ ውሃና ሕክምና አለመስጠት በስፋት መመልከቱን ገልጧል
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በኦሮሚያ እና በሶማሌ ክልሎች የተከሰተውን ድርቅ እና ያደረሰውን ጉዳት ተከትሎ በድርቁ በከፍተኛ ደረጃ ጉዳት ደርሶባቸዋል ተብለው በተለያዩ አካላት በይፋ እውቅና የተሰጣቸው አካባቢዎች በመዘዋወር የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ክትትል በማድረግ ያዘጋጀውን ባለ 50 ገጽ ሪፖርት ባለፈው ሐምሌ 19/2014 ይፋ አድርጓል
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በኦሮሚያ እና በሶማሌ ክልሎች የተከሰተውን ድርቅ እና ያደረሰውን ጉዳት ተከትሎ ከየካቲት 14 እስከ 29 ቀን 2014 ዓ.ም. ድረስ በድርቁ በከፍተኛ ደረጃ ጉዳት ደርሶባቸዋል ተብለው በተለያዩ አካላት በይፋ እውቅና የተሰጣቸው አካባቢዎች በመዘዋወር የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ክትትል በማድረግ ያዘጋጀውን ባለ 40 ገጽ ሪፖርት።  
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በኦሮሚያ እና በሶማሌ ክልሎች የተከሰተውን ድርቅ እና ያደረሰውን ጉዳት ተከትሎ ከየካቲት 14 እስከ 29 ቀን 2014 ዓ.ም. ድረስ በድርቁ በከፍተኛ ደረጃ ጉዳት ደርሶባቸዋል ተብለው በተለያዩ አካላት በይፋ እውቅና የተሰጣቸው አካባቢዎች በመዘዋወር የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ክትትል በማድረግ ያዘጋጀውን ባለ 40 ገጽ ሪፖርት። የሪፖርቱ አንኳር ጉዳዮች (Executive Summary) እዚህ ተያይዟል
ኢሰመኮ የፌዴራል ፣ የኦሮሚያ እና የሶማሌ ክልሎች መንግሥታት በአፋጣኝ ሊተገብሯቸው ይገባል ካላቸው መካከል አንዱ በመረጃና በምዝገባ ሥርዓት የታገዘ፣ አሳታፊ የሆነ፣ የተጠያቂነት ሥርዓት የተዘረጋለት እንዲሁም ከፍላጎት ጋር የተመጣጠነ ምላሽ ማቅረብ፣ ማሰራጨት እና ክትትል ማድረግ የሚለው ነው
የፌዴራል እና የሁለቱ ክልሎች መንግሥታት በአፋጣኝ በመረጃና በምዝገባ ሥርዓት የታገዘ፣ አሳታፊ የሆነ፣ የተጠያቂነት ሥርዓት የተዘረጋለት እንዲሁም ከፍላጎት ጋር የተመጣጠነ ምላሽ ማቅረብ እና ክትትል ማድረግ፣ እንዲሁም በትምህርት፣ በጤና ግልጋሎት እና በመጠለያ መብት ረገድ ያለውን ክፍተት በመለየት መብቶቹን ለማሟላት ተገቢውን እርምጃ በአፋጣኝ መውሰድ እና በመንግሥትና በአጋር ድርጅቶች ለድርቁ የሚሰጡ ምላሾች ለሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች ተጋላጭ የሆኑ የማኅበረሰብ ክፍሎችን ልዩ ፍላጎቶች ከግምት ውስጥ ያስገቡ እንዲሆኑ ማድረግ ይኖርባቸዋል