በኦሮሚያ ክልል በምሥራቅ፣ ምዕራብ እና ቄለም ወለጋ ዞኖች ለሚገኙ ተፈናቃዮች እና ሌሎች የኅብረተሰብ ክፍሎች፥ በቂ፣ ተደራሽ እና ወቅቱን የጠበቀ የምግብ ድጋፍ እንዳልተደረገላቸው፣ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን አስታወቀ
የፌዴራል አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን በበኩሉ የተሟላ እና በቂ ሰብአዊ ድጋፍ ለማድረግ ከፍተኛ የገንዘብ እጥረት ቢኖርም፣ ባለፉት ወራት በመጠለያ ጣቢያዎች ውስጥ ላሉ ተፈናቃዮች ትኩረት በመስጠት በሁለት ዙር ድጋፍ ማድረጉን ተናግሯል ተብሏል
የምግብ ድጋፍ አቅርቦት ወቅቱን የጠበቀ፣ በቂ፣ ተደራሽ እና የሕፃናትን፣ ሴቶችን፣ አካል ጉዳተኞችንና አረጋውያንን ልዩ ፍላጎት ያገናዘበ ሊሆን ይገባል
የንግድ ሥራዎች በአግባቡ መመራታቸው ለሰብአዊ መብቶች መተግበር አወንታዊ አስተዋጽዖ እንዲያበረክቱ ያስችላል
በምግብ ሥርዓት ውስጥ ሰብአዊ መብቶችን መሠረት ያደረገ አቀራረብ (human rights-based approach) መከተል ያስፈልጋል
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን፣ በሶማሌ ክልል የቆሎጂ መጠለያ ማዕከል ውስጥ በሚገኙ ተፈናቃዮች ላይ በተፈጸመ ጥቃት፣ ስድስት ሰዎች እንደተገደሉ አስታውቋል
በሶማሊ እና በኦሮሚያ ክልል አዋሳኝ አካባቢ፣ በሁለቱ ክልሎች የጸጥታ ኃይሎች መካከል በተፈጠረ የተኩስ ልውውጥ ምክንያት በአካባቢው የተጠለሉ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች እና የአካባቢው ነዋሪዎች መጎዳታቸው አሳሳቢ መሆኑን ኮሚሽኑ ጠቅሷል
በተኩስ ልውውጡ ህይወታቸውን ያጡት ሰዎች በቆሎጂ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች መጠለያ ጣቢያ የሚኖሩ እንደነበሩ ኮሚሽኑ ገልጿል
በሶማሌ እና ኦሮሚያ ክልል አዋሳኝ ቦታ በተፈጠረ ግጭት ቢያንስ 6 ሰዎች መገደላቸወን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ገለጸ
በካምፓላ ስምምነት መሠረት የመንግሥት የጸጥታ አካላት የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች የሚገኙባቸውን የመጠለያ ጣቢያዎች ደኅንነት አደጋ ላይ ሊጥሉ ከሚችሉ ተግባራት ሊቆጠቡ ይገባል