የጤና መብት በተሟላ መልኩ እንዲተገበር የመንግሥት እና የሚመለከታቸው አካላትን ትብብር ይጠይቃል
በፍትሕ ሥርዓቱ ውስጥ የጥቃት ተጎጂ ሴቶችና ሕፃናት ሰብአዊ መብቶች አያያዝን ለማሻሻል የፍትሕ አካላት አሠራሮቻቸውን መፈተሽ ይኖርባቸዋል
ኢሰመኮ አቤቱታ አቅራቢዎች እና የመንግስት አካላት ፊት ለፊት ቀርበው የተከራከሩበት ግልጽ ምርመራ በአዳማ አካሂዷል
የግልጽ የምርመራ መድረኩ ተጎጂዎች፣ ባለግዴታዎችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ለሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች እልባት ለማስገኘት እና አስቀድሞ ለመከላከል የመፍትሔ ሐሳቦችን ያመላከተ ነው
ኮሚሽኑ ባወጣው መግለጫ መሠረት "ከቤቶቹ ባለቤቶች ጋር በክፍለ ከተማ፣ በወረዳ እና በቀበሌ ደረጃ ውይይት ተደርጎ በቂ ግንዛቤ" እንዲፈጠር መደረጉን ባለሥልጣናቱ ተናግረዋል
በኦሮሚያ ክልል፣ ዐዲስ በመመሥረት ላይ በሚገኘው በሸገር ከተማ በተፈጸመው ቤቶችን የማፍረስ እና በግዳጅ የማንሣት ርምጃ የተጎዱ ሰዎች፣ በሕጋዊ መንገድ የመኖሪያ ቤት ሊያገኙ እንደሚገባ ኢሰመኮ አሳሰበ
ሚሊዮን ዜጎቿ ተፈናቅለው የችግርና የሰቀቀን ኑሮ እየገፉ ቢሆንም የእነሱን ጉዳይ ጉዳዬ ብሎ የሚሰራ ተቋም የትኛው ነው ብላችሁ ብትፈልጉ አታገኙም
ከሰብአዊ መብቶች አኳያ ሊቀጥሉ እና ሊበረታቱ የሚገባቸው መልካም አሠራሮች ቢኖሩም የአረጋውያን መንከባከቢያ ማእከላቱ በአብዛኛው ቋሚ የገቢ ምንጭ የሌላቸው እና በገቢ ማስገኛ ሥራዎች ላይ ያላቸው ተሳትፎም ውስን መሆኑ አገልግሎታቸውን ለማስቀጠልና ዘላቂነቱን (sustainability) ለማረጋገጥ አሳሳቢ ጉዳይ መሆኑ በሪፖርቱ ተመላክቷል
የመሬት መብት ከምግብ፣ ከጤና፣ ከመጠለያ፣ ከውሃ፣ ከባህላዊ መብቶች ጋር ጥብቅ ግንኙነት ያለው በመሆኑ መሬት ነክ ድንጋጌዎችና ፖሊሲዎች ሰብአዊ መብቶች መር ሊሆኑ ይገባል
«ታጣቂዎቹ ጥቃቱን ባደረሱበት ከተማ ከማኅበረሰቡ ጋር ተቀላቅለው የሚኖሩ ተፈናቃዮችን ቤትለቤት እየዞሩ በተለይ የአማራ ብሔር ተወላጆችን ለይተው ገድለዋል» በማለት የምርመራ ግኝቱ ጠቁሟል