በተፈጥሮ እና ሰው ሠራሽ ምክንያቶች ለሚከሰቱ መፈናቀሎች የሰብአዊ መብቶች መርሖችን የተከተለ ዘላቂ መፍትሔ ማመቻቸት ይገባል
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን የኦሞ ወንዝ ከመጠን በላይ በመሙላቱ እና መደበኛ የመፍሰሻ መስመሩን ለቆ በመውጣቱ ምክንያት በጎርፍ ከተጥለቀለቁ የወንዙ የታችኛው ተፋሰስ አካባቢዎች በተለይም ከዳሰነች ወረዳ የተፈናቀሉ ሰዎችን የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ አስመልክቶ ከጥቅምት 5 እስከ 20 ቀን 2016 ዓ.ም. ክትትል በማከናወን ያዘጋጀውን ባለ 26 ገጽ ሪፖርት ይፋ አድርጓል፡፡ ኢሰመኮ...
ረቡዕ ግንቦት 14 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) በደቡብ ኦሞ ዞን፣ ዳሰነች ወረዳ በሚያዝያ ወር 2012 በወረዳው ግብርና ጽሕፈት ቤት በኩል ምዝገባ የተደረገላቸው 62 ሺህ 790 ተፈናቃዮች ሲሆኑ በኅዳር ወር 2016 ዳግም በተደረገው ምዝገባ የተፈናቃዮች ቁጥር 79 ሺህ 828 ተፈናቃዮች እንደሚገኙ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አስታወቀ
በማሳደጊያ ተቋማት ውስጥ ለሚያድጉ ሕፃናት የሚሰጡ አገልግሎቶች እና እንክብካቤዎች በሕፃናት መብቶች የተቃኙ መሆን አለባቸው
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በአምስት ክልሎች እና በሁለት የከተማ አስተዳድሮች በሚገኙ የመንግሥት እና መንግሥታዊ ባልሆኑ የሕፃናት ማሳደጊያ ተቋማት ውስጥ ያሉ ሕፃናት የሰብአዊ መብቶች ሁኔታን የተመለከተ ባለ 45 ገጽ የክትትል ሪፖርት ይፋ አድርጓል። ኮሚሽኑ በአማራ፣ በሐረሪ፣ በኦሮሚያ፣ በሲዳማ እና በደቡብ ኢትዮጵያ ክልሎች እንዲሁም በአዲስ አበባ እና በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደሮች በሚገኙ 25 የሕፃናት ማሳደጊያ ተቋማት ላይ...

ተፈናቃዮች ዘላቂ መፍትሔ እንዲያገኙ እንዲሁም በመጠለያ ጣቢያዎች በቂ ምግብ፣ ውሃ፣ መጠለያ እና የጤና አገልግሎቶች እንዲቀርቡላቸው ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን ኃላፊነት መወጣት ይጠበቅባቸዋል
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ ጋሞ ዞን፣ በቆላ ሻራ ቀበሌ ውስጥ የደረሰውን የሰብአዊ መብቶች ጥሰት ሁኔታ በሚመለከት ከነሐሴ 22 እስከ 30 ቀን 2015 ዓ.ም. ድረስ በአካባቢው በመገኘት ያደረገውን ምርመራ ይፋ አድርጓል
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ከአስተዳደራዊ መዋቅር ጋር ለተያያዙ አለመግባባቶች አፋጣኝ ሰላማዊ መፍትሔ እንዲፈለግ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን አሳሰበ
በነሐሴ ወር 2015 ዓ.ም. በቆላ ሻራ ቀበሌ ለደረሱ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች ተጠያቂነት ማረጋገጥ እና ከኃይል እርምጃዎች መቆጠብን ጨምሮ፣ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎቶችን በአፋጣኝ ማስጀመር እና በሀገራዊ እና በአካባቢያዊ ጉዳዮች የመሳተፍ መብት ሊረጋገጥ ይገባል