የመንግስት የጸጥታ አካላት በፖለቲካ ፓርቲዎች መሪዎችና አባላት፣ በሚዲያ አባላት እንዲሁም በማህበረሰብ አንቂዎች ላይ ካተኮረ “እስር እና ማዋከብ” እንዲቆጠቡም ኮሚሽኑ ጠይቋል
በፖለቲካ ፓርቲዎች መሪዎችና አባላት፣ በሚዲያ አባላትና በማኅበረሰብ አንቂዎች ላይ ያነጣጠረ የዘፈቀደ እስርና ወከባ ሊቆም ይገባል
በተጠርጣሪዎች ላይ ድብደባና ኢሰብአዊ ድርጊቶችን የሚፈጽሙ የጸጥታ አካላት ላይ ሕጋዊ እርምጃ መውሰድና ተጠያቂነትን ማረጋገጥ ያስፈልጋል
መንግሥት የታራሚዎችን ሰብአዊ መብቶች በማክበር፣ በማስከበር እና በማሟላት ረገድ ቀዳሚ ኃላፊነት አለበት
በሚድያ አዋጁ አንቀጽ 86(1) የተመለከተው የቅድመ እስር ክልከላ ከአዋጁ አንቀጽ 3(1) እና 6(3) ጋርም ተቀናጅቶ ሲነበብ ለተመዘገበ ሚዲያ ብቻ ሳይሆን ለሁሉም ዓይነት ሚዲያዎች የተቀመጠ የሕግ ጥበቃ መሆኑን የሚያመለክት ነው