ሴቶች፣ አካል ጉዳተኞች እና አረጋውያን እንዲሁም የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች በስድስተኛው አጠቃላይ ምርጫ ከነበራቸው ተሳትፎ፣ ተደራሽነት እና አካታችነት አንጻር የተስተዋሉ ክፍተቶችን መለየት ለቀጠይ ምርጫ መሻሻል መሰረት ነው
በኮሚሽኑ የተለዩ ክፍተቶችን ለማስተካከል ሁሉም ባለ ድርሻ አካላት ጥረት ካላደረጉ በቀጣይ ምርጫዎች የዜጎች ሰብአዊ መብቶች በተለይም የመምረጥና የመመረጥ መብት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ማሳደራቸው እሙን ነው
ዶይቼ ቬለ በምርጫው በታዛቢነት ከተሳተፉት የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግሬስ (ኦፌኮ) ሊቀመንበር ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና እና የኢትየጶጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ኮሚሽነር (ኢሰመኮ) ዶ/ር ዳንኤል በቀለ ትዝብታቸውን ተጋርቷል