በአማራ ክልል እየተካሄደ ያለው ወታደራዊ እንቅስቃሴ የንፁሃን ዜጎችን ህይወት እየቀጠፈ ነው ተብሏል
በአማራ ክልል፣ “የሕግ ማስከበር” በሚል በፌዴራሉ መንግሥት እየተወሰደ ያለው ወታደራዊ ርምጃ፣ በጣም አሳሳቢ እንደኾነና ችግሩ በውይይት እንዲፈታ፣ ኢሰመኮ የተወካዮች ምክር ቤትን አሳሰበ
በአማራ ክልል እየተደረገ ባለው “የጸጥታ እርምጃ” የተፈጠረው ጉዳት ሳይባባስ፤ ፓርላማው የሰላማዊ መፍትሔ አስፈላጊነትን ለመንግስት የስራ አስፈጻሚ አካል “በአስቸኳይ እንዲያሳስብ” የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ጥያቄ አቀረበ
በኢትዮጵያ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት በሰብአዊ መብት ጥሰት ፈፅሞ ተጠያቂ የሚሆን አካል የለም የሚለው እንዳሳሰባቸው ተናግረዋል
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን በተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች የሰብአዊ መብት ጥሰት እንዳይፈፀም በግንዛቤ ማስጨበጫ ተግባራት ላይ ማተኮር እንዳለበት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴው ጠቁሟል
ሙሉ ቪዲዮውን ይመልከቱ
Human rights commission calls on government to stop arbitrary arrests of journalists and to respect citizens’ rights in addition to lifting the internet restriction imposed on social media as it is violation of the human rights principle
በአማራ ክልል ያለው ወታደራዊ እርምጃና የሰብአዊ መብቶች እንደምታው፣ የዘፈቀደ እስርና ተገቢ ያልሆነ አያያዝ፣ ተመጣጣኝ ያልሆነ የኃይል አጠቃቀም፣ በሚዲያና ተቃዋሚዎች ላይ ያነጣጠረ ጥቃት፣ ከቦታ ወደ ቦታ መንቀሳቀሰ መብት ላይ የተጣለ የዘፈቀደ ገደብ፣ ሕጋዊ ሂደትን ያልተከተለ የቤቶች ፈረሳ፣ በግዳጅ ማስነሳትና የኑሮ ውድነት የተነሳ የደረሰው እንግልትና የማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ መብቶች ጥሰቶች እንዲሁም በጦርነት የተጎዱ አካባቢዎችን መልሶ ማቋቋም አሳሳቢነታቸው ከቀጠሉ ጉዳዮች ውስጥ ይገኛሉ