የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በተለይም በአራት ክልሎች መንግሥት እና ታጣቂ ኃይሎች በሚወስዷቸው እርምጃዎች እና ጥቃቶች ከቦታ ቦታ የመዘዋወር ነጻነት መብት አደጋ ላይ መውደቁን ተገንዝቢያለሁ ብሏል
መንግሥት በተለያዩ ቦታዎች የተፈጸሙ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች ላይ የተሟላ ማጣራት በማድረግ ተጠያቂነትን ሊያረጋግጥ እንዲሁም በድርጊቶቹ ተጎጂ ለሆኑ ሰዎች ፍትሕ ሊያሰፍን ይገባል
የመንቀሳቀስ ነጻነት ምንድነው? የመንቀሳቀስ ነጻነት በውስጡ ምን ምን ጥበቃዎችን ይዟል? የመንቀሳቀስ ነጻነት ላይ የሚጣሉ ገደቦች ምን ሁኔታዎችን ማሟላት አለባቸው? የመንቀሳቀስ ነጻነትን ከማረጋገጥ አንጻር የመንግሥታት ግዴታዎች ምንድን ናቸው? 
በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ “ቃሊቲ አካባቢ” ተብሎ በሚጠራው የአሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ አካባቢ ባለ 'ሰፊ መጋዘን' ውስጥ፤ ከጎዳና ላይ የተነሱ በርካታ ሰዎች መኖራቸውንና ይህ ሰዎችን የመያዝና ወደ ማቆያ ማዕከል የማስገባት ድርጊት አሁንም መቀጠሉን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አስታውቋል
ከጎዳና ላይ ለሚነሱና ወደማቆያ ለሚገቡ ሰዎች ሰብአዊ መብቶችን ያማከለ ዘላቂ መፍትሔ መስጠት ያስፈልጋል
ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ወይም በሕጋዊ መንገድ ሀገሪቱ ውስጥ የሚገኝ የውጭ ዜጋ በመረጠው የሀገሪቱ አካባቢ የመዘዋወርና የመኖሪያ ቦታ የመመሥረት፣ እንዲሁም በፈለገው ጊዜ ከሀገር የመውጣት ነጻነት አለው
Any Ethiopian or foreign national lawfully in Ethiopia has, within the national territory, the right to liberty of movement and freedom to choose his residence, as well as the freedom to leave the country at any time he wishes to