ኮሚሽኑ በግጭቱ በሲቪሎች ላይ ጉዳት መድረሱ መረጃ ደርሶኛል ብሏል
የኢትዮጵያ መንግስት በቅርቡ በአማራ ክልል በሙሉ እንዲሁም በመላው ሀገሪቱ እንደአስፈላጊነቱ ተፈጻሚ የሚሆን እና ለስድስት ወራት የሚቆየው አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ተፈጻሚነት በአማራ ክልል ብቻ እንዲገደብ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን አሳሰበ። ፤ ኮሚሽኑ የአፈጻጸም ጊዜው ወደ አንድ ወር እንዲያጥርም ምክረ ሃሳብ አቅርቧል
በአማራ ክልል በመከላከያና በታጣቂ ሚሊሻዎች፣ ፋኖ የተነሳው ግጭት መባባሱን ተከትሎ የተደነገገው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለሰብዓዊ መብቶች መከበር ቅድሚያ መስጠት እንደሚገባ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አሳሰበ
ሁሉም ወገኖች ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት ለሰላም አማራጮች ቅድሚያ እንዲሰጡ፣ ግጭቱን ከሚያባብሱ ድርጊቶች እንዲቆጠቡ፣ የክልሉን ሰላም እና ደኅንነት ለማረጋገጥ በመንግሥት የሚወሰዱ እርምጃዎች በማናቸውም ሁኔታ ቢሆን ነዋሪዎችን ለበለጠ ጉዳት እና ለሰብአዊ መብቶች ጥሰት እንዳይዳርጉ ተገቢው ጥንቃቄ እንዲደረግ ያሳስባል