States Parties shall seek lasting solutions to the problem of displacement by promoting and creating satisfactory conditions for voluntary return, local integration or relocation on a sustainable basis and in circumstances of safety and dignity
ተዋዋይ ሀገራት በዘላቂነት እና ደኅንነትንና ክብርን በጠበቀ መልኩ በፈቃደኝነት ላይ የተመሠረተ የመመለስ፣ ከአካባቢ ማኅበረሰብ ጋር ተዋሕዶ የመኖር ወይም ወደ ሌላ ቦታ የማስፈር መፍትሔዎችን ለማመቻቸት አጥጋቢ የሆኑ ሁኔታዎች በማበረታታትና በመፍጠር ለመፈናቀል ችግር ዘላቂ መፍትሔዎችን ማፈላለግ አለባቸው
የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮችን ወደቀድሞ ቀያቸው የመመለስ እና ዘላቂ መፍትሔ እንዲያገኙ የማድረግ ሂደት ሰብአዊ መብቶችን መሠረት ያደረገ መሆኑን ማረጋገጥ ያስፈልጋል
Effective collaboration and coordination among stakeholders are essential to ensure the protection of the rights of people on the move
ስደተኞች፣ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች፣ ጥገኝነት ጠያቂዎች እና ፍልሰተኞች የሚያስፈልጓቸው ሰነዶችን ተደራሽ ለማድረግ የባለድርሻዎች የተቀናጀ ትብብር አስፈላጊ ነው
ለሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች የሰብአዊ መብቶች ጥበቃ እና ድጋፍ ለማድረግ የተዘጋጀው ረቂቅ ብሔራዊ ሕግ የሚስተዋሉ ክፍተቶችን ለመሙላት ጉልህ ፋይዳ አለው
EHRC Participated in a side event on the Rights of Persons with Disabilities hosted by Global Alliance of National Human Rights Institutions (GANHRI) in Geneva
በኦሞ ወንዝ የላይኛው ተፋሰስ አካባቢዎች ከነሐሴ ወር የመጀመሪያ ቀናት ጀምሮ በጣለው ከፍተኛ መጠን ያለው ዝናብ ምክንያት የዳሰነች ወረዳ ዋና ከተማ በሆነው የኦሞራቴ ከተማ እንዲሁም ቻይና ካምፕ በተባሉ የተፈናቃይ መጠለያ ጣቢያዎች ላይ በውሃ የመጥለቅለቅ ሥጋት ተጋርጦባቸዋል ብሏል
በኢትዮጵያ በተፈጥሮ አደጋዎች ምክንያት የሚደርስ መፈናቀል እየተስፋፋ በመምጣቱ ይህን መሰል ሥጋት ያለባቸውን አካባቢዎች በመለየት እና በጉዳቱ ልክ ምላሽ ለመስጠት የሚያስችል በቂ ቅድመ ዝግጅት ማድረግ ያስፈልጋል
የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች በቂ እና ወቅቱን የጠበቀ የምግብ ድጋፍ እየቀረበላቸው ባለመሆኑ ለረሀብ አደጋ እየተጋለጡ ናቸው