የፌዴራል አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን በበኩሉ የተሟላ እና በቂ ሰብአዊ ድጋፍ ለማድረግ ከፍተኛ የገንዘብ እጥረት ቢኖርም፣ ባለፉት ወራት በመጠለያ ጣቢያዎች ውስጥ ላሉ ተፈናቃዮች ትኩረት በመስጠት በሁለት ዙር ድጋፍ ማድረጉን ተናግሯል ተብሏል
የኢትዮጵያ መንግሥት፣ ዜጎችን በአፈናቀሉና ልዩ ልዩ ጉዳቶችን በአደረሱ አካላት ላይ ተጠያቂነት ባለማስፈኑ፣ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች ፍትሕ የማግኘት መብት እንደተፈነጋቸው፣ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ባወጣው ዓመታዊ ሪፖርቱ አስታወቀ
የተፈናቀሉ ሰዎች ከመንግሥት አካላት ጥበቃ እና ሰብአዊ ድጋፍ የመጠየቅ እና የማግኘት መብት አላቸው። ይህን ጥያቄ በማቅረባቸው ሊከሰሱ ወይም ሊቀጡ አይገባም
ዜጎችን ከመደበኛ የመኖሪያ ቦታቸው ያፈናቀሉ፣ የሰው ሕይወት ያጠፉ፣ ሀብት ያወደሙ፣ አካላዊ ጉዳት ያደረሱ ቡድኖችና ግለሰቦች በሕግ ተጠያቂ ለማድረግ በቂ ዕርምጃዎች ባለመወሰዳቸው የሕግ በላይነት፣ ተጠያቂነትንና የተፈናቃዮችን ፍትሕ የማግኘት መብት የሚነፍግ ነው ሲል፣ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አስታወቀ
ይህ ሁለተኛው የዘርፍ ሪፖርት ኢሰመኮ ሐምሌ 5 ቀን 2015 ዓ.ም. ይፋ ካደረገው የኢትዮጵያ ዓመታዊ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ሪፖርት ላይ በተጨማሪነት ኮሚሽኑ የተፈናቃዮች የሰብአዊ መብቶች አያያዝን በተመለከተ የለያቸውን መልካም ጅማሮዎች፣ አሳሳቢ ሁኔታዎችንና ምክረ ሐሳቦችን አካቷል
ለጋሾች ለስደተኞች የጀመሩት ርዳታ በሦስተኛ ወገን እንደሚታደል ኢትዮጵያ አስታወቀች
መንግሥት ለተፈናቃዮች ጥበቃ እና ድጋፍ የሚሰጥና የሚያስተባብር በግልጽ ሥልጣን የተሰጠው ተቋም በማቋቋም ወደ ሥራ ማስገባት ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ተግባር ነው
The meeting concluded by highlighting progress, challenges, and opportunities in strengthening government leadership for implementing durable solutions for IDPs in Ethiopia
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን፣ በሶማሌ ክልል የቆሎጂ መጠለያ ማዕከል ውስጥ በሚገኙ ተፈናቃዮች ላይ በተፈጸመ ጥቃት፣ ስድስት ሰዎች እንደተገደሉ አስታውቋል
በሶማሊ እና በኦሮሚያ ክልል አዋሳኝ አካባቢ፣ በሁለቱ ክልሎች የጸጥታ ኃይሎች መካከል በተፈጠረ የተኩስ ልውውጥ ምክንያት በአካባቢው የተጠለሉ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች እና የአካባቢው ነዋሪዎች መጎዳታቸው አሳሳቢ መሆኑን ኮሚሽኑ ጠቅሷል